በኡጋንዳ የቆሻሻ መጣያ በደረሰ የመሬት መንሸራተት የ24 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ1,000 በላይ ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት ደረሰ

ሰብስክራይብ
በኡጋንዳ የቆሻሻ መጣያ በደረሰ የመሬት መንሸራተት የ24 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ1,000 በላይ ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት ደረሰየመሬት መንሸራተቱ በሉሳንጃ፣ ኪቲቲካ እና ኪቲኤዚ መንደሮች ላይ ጉዳት አድርሷል። "ሶስቱም መንደሮች ከ1,000 በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ይገመታል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እና በኡጋንዳ ቀይ መስቀል ማህበር በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የተመዘገቡት የተፈናቃዮች ቁጥር እስካሁን 56 አባወራዎች ደርሷል" ሲል ሊሊያን አበር የዕርዳታና የአደጋ ዝግጁነት ሚኒስትር ዴኤታ ለፓርላማ ተናግረዋል። ምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ማቅረባችንን እንቀጥላለን፤ መንግስት የካሳ ክፍያን ዝርዝር ሁኔታ እያጠና ይገኛል። "መንግስት የቆሻሻ አወጋገድን ለማሻሻል በማቃጠል፣ መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል እና በኃይል ማመንጫነት ለመጠቀም እያደረገ ያለውን ጥረት ሚንስትሯ አመልክተዋል።ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ምርመራ እንዲደረግ ትእዛዝ የሰጡ ሲሆን፤  በቆሻሻ መጣያው አቅራቢያ ያሉ አባወራዎች እንዲነሱም መመሪያ ሰጥተዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0