በሱዳን ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ሳቢያ ወደ 70 የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታወቁ

ሰብስክራይብ
በሱዳን ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ሳቢያ ወደ 70 የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታወቁየሱዳን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ካሊል ፓሻ ሳይሪን "በጎርፍና በዝናብ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 68 ደርሷል" ማለታቸውን የሱዳን ዜና አገልግሎት ማክሰኞ ዘግቧል።ተጎጂዎቹ በተለያዩ ምክንያቶች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የቤት መደርመስና መስጠም ይገኙበታል። ሚኒስትሩ አያይዘውም በሀገሪቱ ዝናባማ ወቅት በተከሰተው የጎርፍ አደጋ 130 ሰዎች መቁሰላቸውን እና ከ4,000 በላይ ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ጠቁመዋል።በሱዳን የዝናብ ወቅት በየአመቱ በሰኔ ወር ይጀምርና እስከ ጥቅምት ወር ድረስ ይቆያል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0