እስራኤል እ.አ.

ሰብስክራይብ
እስራኤል እ.አ.አ ከነሐሴ 1 እስከ 11 ባሉት ቀናት ወደ ጋዛ መግባት የነበረበትን አንድ ሶስተኛ ያህል እርዳታ እንዳይገባ ከልክላለች ሲል ኦቻ ተናግሯል እ.አ.አ "ከነሐሴ 1 እስከ 11 ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ሰሜናዊ ጋዛ ከተደረጉት 85 የተቀናጁ የሰብአዊ እርዳታ ተልእኮዎች መካከል 34ቱ ብቻ በእስራኤል ባለስልጣናት እንዲገቡ የተመቻቸ ሲሆን የተቀሩት በፀጥታ በሎጅስቲክስ እና በአሰራር ምክንያቶች ወይ ተከልክለዋል ወይም ተሰርዘዋል።" ሲል ኦቻ በዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተናግሯል።በደቡብ ፍልስጤም ግዛት እስራኤል ከ122 ተልዕኮዎች ውስጥ 63ቱን ብቻ ፈቅዳለች ሲል ድርጅቱ ጨምሮ ገልጿል። "የእነዚህ የመዳረሻ ገደቦች ድምር ውጤት በከፍተኛ ግጭት እና ሰላም ማጣት መባባሱ እና በሰሜን እና በደቡብ እስራኤል መካከል የገጠመው የመንቀሳቀስ ተግዳሮት እና በተደጋጋሚ የሚተላለፈው የልቀቁ ትእዛዝ፤ በሰዎች ላይ ሞት፣ ህመም፣ ረሃብ፣ እና ጥማት በየእለቱ እንዲመዘገብ አድርጓል።"ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0