የነሀሴ 8 ረፈድ ዋና ዋና የአለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የነሀሴ 8 ረፈድ ዋና ዋና የአለም ዜናዎች🟠 ኢትዮጵያ ለኬንያ የምታቀርበውን የኤሌክትሪክ ሀይል ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ88% መጨመሩን የኬንያ ኢነርጂ አውታር ገልጿል።🟠 የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በግብፅ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው። ከአንድ ቀን በፊት ግብፅ በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ኤምባሲዋን ከፍታለች።🟠 የአየር መከላከያ ሃይሎች አራት ታክቲካል ሚሳኤሎችን እና 117 ድሮኖችን በሩሲያ ክልሎች በአንድ ምሽት መትተው መጣላቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቋል።🟠 የተባበሩት መንግስታት ተወካዮች ኪየቭ በኩርስክ ክልል የፈፀመችው ድርጊት በሽብርተኝነት የተፈረጀ መሆኑን መረዳት አለባቸው። ተስፋ የምናደርገው፤ ክልሉን ለመቆጣጠር ድረስ ያላቸውን ፍላጎት በእነሱ አቅም" መፈጸም የሚቻል አይደለም። " ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኦፊሴላዊ ተወካይ ዛካሮቫ ተናገረዋል።🟠 የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪሺዳ የገዥው ፓርቲ መሪ ሆነው ለሁለተኛ ጊዜ እንደማይወዳደሩ አረጋግጠዋል።🟠 የግብፅ እና የኳታር ሸምጋዮች ሀማስ በጋዛ የእርቅ ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን የሚያመለክት መልእክት ለእስራኤል አስተላልፏል ሲል ሁሪየት የተሰኘው የቱርክ ጋዜጣ ዘግቧል።🟠 የሩሲያ መከላከያ ሚንስትር ቤሉሶቭ በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ዞን ውጤታማ መሆናቸውን ያረጋገጡ የጦር መሳሪያዎች ናሙና በሞስኮ እየተካሄደ ባለው የ"ሰራዊት" መድረክ ላይ አቅርበዋል። የተማረኩ የጦር መሣሪያዎችን በእይታ እንዲቀርቡ ተደርጓል።🟠 ከ25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ትራምፕ ከማስክ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ሙሉ ለሙሉ አዳምጠዋል ሲል የሪፐብሊካኑ የዘመቻ ዋና መስሪያ ቤት የማህበራዊ ሚዲያ ስታቲስቲክስን ጠቅሶ ዘግቧል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0