የነሐሴ 7 ምሽት ዋና ዋና የአለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የነሐሴ 7 ምሽት ዋና ዋና የአለም ዜናዎች🟠 የአፍሪካ ህብረት የጤና ጥበቃ ቡድን በአህጉሪቱ እየተባባሰ በመጣው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ምክንያት የህዝብ ጤና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል።🟠 ፑቲን ከፍልስጤም መሪ ማህሙድ አባስ ጋር ያደረጉት ውይይት መጠናቀቁን ክሬምሊን አስታውቋል። ልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ቢቀጥልም፤ ሩሲያ ለመካከለኛው ምስራቅ ክስተቶች ትኩረት መስጠቷን ትቀጥላለች ሲሉ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ተናግረዋል።🟠 በኩርስክ ክልል በዩክሬን ሀይሎች ላይ በደረሰው ጉዳት በቀን እስከ 420 የሚደርሱ ወታደሮች መሞታቸውን እና 55 መሳሪያ የታጠቁ ተሽከርካሪዎች ደግሞ መውደማቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።🟠 የዩክሬን ጦር በሊሲቻንስክ ክልል አውቶቡስ ገጭቷል። በግጭቱ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ 28 ደግሞ መቁሰላቸውን የሊሲቻንስክ ሕዝቦት ሪፐብሊክ ኃላፊ ፓሴችኒክ ገልጿል።🟠 ፖላንድ 96 AH-64E Apache ሄሊኮፕተሮችን ከአሜሪካ መግዛት የሚያስችላት የ10 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ስምምነቱ ማክሰኞ ዕለት ተፈራርማለች።🟠 የቶኪዮ ነዋሪዎች በናንካይ ገንዳ አካባቢ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ስጋት ሊፈጠር እንደሚችል ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ተከትሎ ሩዝ እና ውሃ ለመግዛት ተጣድፈዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0