ከ11,000 በላይ ሰዎች ከሩሲያዋ ቤልጎሮድ ክልል ድንበር ለቀው ወጥተዋል

ሰብስክራይብ
ከ11,000 በላይ ሰዎች ከሩሲያዋ ቤልጎሮድ ክልል ድንበር ለቀው ወጥተዋልበአሁኑ ጊዜ ወደ 1,000 የሚጠጉ ሰዎች በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ የቤልጎሮድ ክልል ገዥ ቪያቼስላቭ ግላድኮቭ ተናግረዋል።ሰኞ እለት የክራስኖያሩዝስኪ አውራጃ ነዋሪዎች በዩክሬን ጦር ኃይሎች እንቅስቃሴ ምክንያት ወደ ደህንነታቸው ወደተጠበቁ አካባቢዎች እየተወሰዱ መሆኑን ተገልጿል።ባለፈው ሳምንት የዩክሬን ጦር ወደ ሩሲያ ድንበር አቋርጦ በኩርስክ ክልል ላይ ጥቃት ፈጽሞ በርካታ መንደሮችን መያዙ ይታወቃል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጥቃቱ ላይ አስተያየት ሲሰጡ ዩክሬን ሌላ መጠነ ሰፊ የሆነ ትንኮሳ ፈፅማለች፤ ያለ ልዩነት ንፁሃን ዜጎችን ኢላማዎች አድረጋ ጥቃት ፈፅማለች ብለዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0