የነሐሴ 7 ረፈድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የነሐሴ 7 ረፈድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች🟠 በአሁኑ ወቅት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ያለው የአፍሪካ ሀገራት ውክልና በምንም መልኩ የአፍሪካ አህጉር በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ካላት ዘመናዊ ሚና ጋር አይመጣጠንም ሲሉ በመንግስታቱ ድርጅት የሩሲያ ተቀዳሚ ምክትል ቋሚ ተወካይ ዲሚትሪ ፖሊያንስኪ ገለፁ። 🟠 የኬንያ የገንዘብ ሚኒስቴር ከሳምንታት ህዝባዊ ተቃውሞ በኋላ የሀገሪቱ ህግ አውጭዎች ተገድደው ውድቅ ያደርጉትን የታክስ ማሻሻያዎችን ወደነበሩበት ለመመለስ እየሰራ ነው።🟠 የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች አዛዥ ጄኔራል ዳጋሎ እሮብ እለት በስዊዘርላንድ በሚጀመረው የተኩስ አቁም ድርድር የሀገሪቱ መደበኛ ታጣቂ ሃይሎች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል። አሜሪካ ቀደም ሲል የካርቱም መንግስት ባይሳተፍ እንኳን ውይይቱን እንደሚካሄድ ተናግራለች።🟠 ዩክሬን የኩርስክን ግዛት በማጥቃት ቀይ መስመሩን ጥሳለች ሲሉ በሩሲያ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር ጆን ሱሊቫን ተናግዋል።🟠 ዋይት ሀውስ የቀድሞው የዩክሬን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር አርሰን አቫኮቭ ዘሌንስኪን ለመተካት እጩ አድርጎ እንደሚመለከታቸው የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት ገልጿል።🟠 የሩሲያ አየር መከላከያ ዘዴዎች በኩርስክ፣ ቤልጎሮድ እና ቮሮኔዝ ክልሎች ላይ በአንድ ጀምበር 14 ድሮኖችን ማውደሙን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቋል።🟠 ትረምፕ ፑቲንን እንደ "ጥሩ ተደራዳሪ" እንደሚቆጥሩ ገልፀው ባይደን ግን ዩክሬን ኔቶ የምትቀላቀልበትን እድል በመፍቀድ "ስህተት ፈፅሟል።" ብለዋል።🟠 ኤሎን ማስክ ከትራምፕ ጋር ትላንት ሌሊት ቃለ ምልልስ ካካሄደ በኋላ  ከካማላ ሃሪስ ጋርም ተመሳሳይ ቃለ ምልልስ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0