ሰርቢያ ብሪክስን እንደ ጥሩ ዕድል እንደምትመለከት እና የአውሮፓ ህብረት ትክክለኛ አማራጭ እንደሆነ የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ሰርቢያ ብሪክስን እንደ ጥሩ ዕድል እንደምትመለከት እና የአውሮፓ ህብረት ትክክለኛ አማራጭ እንደሆነ የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ቩሊን ብሪክስ ከሰርቢያ የሚፈልገው አንዳች ነገር እንደሌለ እና ከሚጠየቀው በላይ የሚሰጠው ብዙ እንደሆነ ተናግረዋል። "ይህ ድርጅት ከሰርቢያ የሚጠይቀው ምንም ነገር የለም፡፡ ነገር ግን እኛ ከምንፈልገው በላይ መስጠት ይችላል፡፡ የአውሮፓ ህብረት ከእኛ ሁሉኑም ነገር ይፈልጋል። ይሁንና ህብረቱ ስለሚፈይድልን ነገር እርግጠኛ አይደለሁም። ብሪክስ እድላችንና ትክክለኛው አማራጫችን ነው፡፡ እኔ ሰርቢያ ሁሉኑም የብሪክስ አማራጮች እንድትመለከት እና ከድርጅቱ አባል ሀገራት ጋር የተቀራረበ ትብብር እንድትፈጥር እመርጣለሁ" ሲሉ ከስፑትኒክ ጋር በነበራቸው ቆይታ አብራተዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም የሰርቢያ ባለስልጣናት በሩሲያ ካዛን ለሚካሄደው 14ኛው የብሪክስ ጉባኤ ኦፊሴላዊ ጥሪ በቀጣይ ቀናት ይደርሳቸዋል ብለው እንደሚጠብቁ ገልጸዋል። የብሪክስ ዓመታዊ ጉባኤ እ.አ.አ ከኦክቶበር 22 እስከ 24 በካዛን ይካሄዳል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0