በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ የቆሻሻ መጣያ ቦታ ላይ በደረሰ የመሬት መደርመስ አደጋ ቢያንስ 23 ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ

ሰብስክራይብ
በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ የቆሻሻ መጣያ ቦታ ላይ በደረሰ የመሬት መደርመስ አደጋ ቢያንስ 23 ሰዎች መሞታቸው ተዘገበየቆሻሻ መጣያው ክፍል ቅዳሜ ማለዳ እንደተደረመሰ ሞኒተር ጋዜጣ ዘግቧል። የፍለጋ እና ማዳን ስራው አሁንም ቀጥሏል፡፡የኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ባለስልጣን ቃል አቀባይ ዳንኤል ኑዌ አቢኔ እንደተናገሩት ከቆሻሻ ቁልል ስር በፍለጋ የወጡ 14 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ሙላጎ ብሔራዊ ሪፈራል ሆስፒታል ገብተው አስፈላጊው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ አንዳንዶቹ ከወዲሁ ከሆስፒታል ወጥተዋል፡፡የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ፖሊሶች፣ የኡጋንዳ ብሔራዊ መንገዶች ባለስልጣን እና የኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ባለስልጣን ሰዎችን ለማዳን እንዲሁም የሟቾች አስክሬን ለመፈለግ ተባብረው እየሰሩ እንደሆነም ተዘግቧል፡፡የካምፓላ ከንቲባ ኤሪያስ ሉክዋጎ የቆሻሻ ማጠራቀሚያው ስፍራው ሊደረመስ እንደሚችል በጥር ወር አስጠንቅቀው ነበር ተብሏል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0