ፑቲን በሩሲያ እየተካሄደ በሚገኘው የአርሚ-2024 መድረክ ለተሳታፊዎች ንግግር አድርገዋል

ሰብስክራይብ
ፑቲን በሩሲያ እየተካሄደ በሚገኘው የአርሚ-2024 መድረክ ለተሳታፊዎች ንግግር አድርገዋል የንግግራቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡- ◻ ሩሲያ ከአጋሮቿ ጋር ላላት ግንኙነት ዋጋ ትሰጣለች፤ ለማሳደግም ዝግጁ ነች። እንዲህ ዓይነት አመለካከቶች በስፋት ይንጸባረቃሉ፤ እውነተኛ ምላሽም ያገኛሉ። ◻ የሀገር ውስጥ የጦር መሳርያ እውቀቶች በጦር ግንባሩ ላይ ውጤታማ እንደሆኑ እያስመሰከሩ እና ደረጃቸውም በየግዜው እየተሻሻለ ይገኛል። ◻ የመከላከያ ኢንዱስትሪው እንቅስቃሴ ከአነስተኛ ቢዝነሶች፣ ከህዝብ ድርጅቶች፣ ከበጎ ፈቃደኞች እና ከዜጎች ከፍተኛ ድጋፍ ያገኛል። ◻ መድረኩ የዘመናዊ መሳሪያ ክፍሎች፣ የመገናኛ ዘዴዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ጦርነት እና ጥበቃ፣ ሰው አልባ ስርዓቶች እና ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ቴክኖሎጂዎችን ቅድሚያ ይሰጣል። ◻ በፎረሙ አዳዲስ ተስፋ ያላቸውው ግንኙነቶች ይመሰረታሉ፣ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ውሎች ይፈጸማሉ እንዲሁም የወዳጅ ሀገራት በጸጥታ ዘርፍ ያላቸው ግንኙነት የበለጠ ውጤታማ ይሆናል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0