የነሐሴ 6 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡- 🟠 ሱዳን በዚህ ሳምንት ስዊዘርላንድ ውስጥ በሚካሄደው የሰላም ድርድር የሚኖራትን ተሳትፎ በተመለከተ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በሳውዲ ከተማ ጀዳ ሲካሄድ የነበረው ምክክር ያለ ስምምነት እንደተጠናቀቀ ካርቱም አስታውቃለች። 🟠 የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ አዲስ ፕሬዝዳንታዊ የስልጣን ጊዜያቸውን በይፋ ጀመሩ። 🟠 የዛፖሮዥያ የኒውክሌር ሃይል ማመንጫ ማቀዝቀዣ ማማ በሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ቢቃጣጠልም የመፍረስ ስጋት እንደሌለበት የጣቢያው ቃል አቀባይ ገልጸዋል። 🟠 የሩሲያ አየር መቃወሚያ 18 የዩክሬን ጀት ዓይነት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን 11 በኩርስክ ክልል፣ 5 በቤልጎሮድ ክልል እና 2 በቮሮኔዝ ክልል ላይ በአንድ ሌሊት እንዳወደሙ የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል። 🟠 በስሎቫክ ጠቅላይ ሚኒስትር ፊኮ እና በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ ከተደረገው የግድያ ሙከራ በኋላ የሰርቢያው ፕሬዝዳንት ቩቺችም በዩክሬን ዙርያ በያዙት አቋም አደጋ ላይ ናቸው ሲሉ የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ቩሊን ተናግረዋል። 🟠 ዶናልድ ትራምፕ ከቢልየኔር ኤለን መስክ ጋር ነሐሴ 6 የሚያደርጉት ቃለ ምልልስ በምስራቃዊ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2፡00 ላይ ይደረጋል የተባለ ሲሆን “የክፍለ ዘመኑ ውይይት” እንደሚሆን የትራምፕ ዘመቻ እሁድ እለት ገልጿል። 🟠 የሩሲያ "አርሚ-2024" መድረክ በሞስኮ አቅራቢያ በምትገኘው ኩቢንካ ከተማ ተጀመረ። ከ83 ሀገራት የተውጣጡ ልዑካን በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ 39ቱ በመከላከያ ዲፓርትመንት ኃላፊዎች እና በጠቅላይ ኤታማዦር ሹሞች እየተመሩ መሆናቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የነሐሴ 6 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-
የነሐሴ 6 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-
Sputnik አፍሪካ
የነሐሴ 6 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡- 🟠 ሱዳን በዚህ ሳምንት ስዊዘርላንድ ውስጥ በሚካሄደው የሰላም ድርድር የሚኖራትን ተሳትፎ በተመለከተ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በሳውዲ ከተማ ጀዳ ሲካሄድ የነበረው ምክክር ያለ ስምምነት እንደተጠናቀቀ ካርቱም... 12.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-12T12:27+0300
2024-08-12T12:27+0300
2024-08-12T12:46+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий