የጋና ሶሻሊስት ንቅናቄ ዩክሬን በማሊ እና በሰፊው ምዕራብ አፍሪካ ለአማፂ ቡድኖች የምታደርገውን ድጋፍ አወገዘ

ሰብስክራይብ
የጋና ሶሻሊስት ንቅናቄ ዩክሬን በማሊ እና በሰፊው ምዕራብ አፍሪካ ለአማፂ ቡድኖች የምታደርገውን ድጋፍ አወገዘ የጋና ሶሻሊስት ንቅናቄ (ኤስ.ኤም.ጂ) ዩክሬን ድርጊቷን ከሩሲያ ጋር እየተደረገ ያለው ግጭት ትክክለኛ ቅጥያ ነው ማለቷን ውድቅ በማድረግ የዩክሬንን ተግባር “ህገ-ወጥ” “ቅኝ አገዛዛዊ እና ዘረኛ” ብሎታል። "አፍሪካውያን ከሩሲያ ጋር ግኑኝነት ለመፍጠር የዩክሬንንም ሆነ የምዕራባውያንን ይሁንታ አይፈልጉም። (በእነዚያ ክፉ የቅኝ ግዛት ዘመናትም እንኳ ሩሲያ አፍሪካ ውስጥ ምንም አይነት የይገባኛል ጥያቄ አልነበራትም)። ዩክሬን አፍሪካ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት መብት እንዳላት መናገሯ ግልጽ እና ቀላል በሆነ መንገድ የአፍሪካ ህዝብ ጠላት ያደርጋታል" ሲል ንቅናቄው እሁድ እለት በመግለጫው ተናግሯል። ኔቶ የዩክሬንን ድርጊት በማመቻቸት ሃላፊነት ይወስዳል ያለው ንቅናቄው "በፍልስጤም የእስራኤል ሰፋሪዎች ከሚፈፅሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል" ጋር አነጻጽሮታል። ኤስኤምጂ ዩክሬን ለምዕራባውያን ሀይሎች ተላላኪ ሆና እየሰራች ነው ብሎ እንደሚያምን ገልፆ የሳህል ቀጠናን የማተራመስ አጀንዳ እያስቀጠለች ነው ብሏል። "ኤስኤምጂ የሴኔጋል፣ ማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪናፋሶ መንግሥታት ለዚህ ንቀት የሰጡትን ምላሽ እና የዩክሬን ዲፕሎማቶች ከሀገራቸው እንዲወጡ መጠየቃቸውን ሙሉ በሙሉ ይደግፋል" ሲል ጋዜጣዊ መግለጫው አትቷል። ንቅናቄው አክሎም “ኤስኤምጂ የጋና መንግሥት፣ ኢኮዋስ እና የአፍሪካ ኅብረት ትንኮሳውን በዝምታ ማለፋቸውን ይቃወማል። ሀገራዊና አህጉራዊ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ እና ቢያንስ ይህን ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ለውይይት እንዲያቀርቡ እንጠይቃለን" ብሏል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0