አልጄሪያ እና ቱኒዚያን የሚያገናኘው የባቡር መስመር ከ30 ዓመታት ቆይታ በኋላ በይፋ ስራ ጀመረ

ሰብስክራይብ
አልጄሪያ እና ቱኒዚያን የሚያገናኘው የባቡር መስመር ከ30 ዓመታት ቆይታ በኋላ በይፋ ስራ ጀመረ የአልጄሪያ ባቡር ትራንስፖርት ኩባንያ አገልግሎቱ በድጋሚ እንደጀመረና የመጀመሪው የባቡር ጉዞ እሁድ ከቱኒዝ እንደተነሳ ገልጿል። 357 ኪሎ ሜትር እርቀት የሚሸፍነው የባቡር መስመር በአልጄሪያ አናባ ከተማ እና በቱኒዚያ ዋና ከተማ ቱኒዝ መካከል የሚገኙ በርካታ ከተሞችን በማለፍ በቀን አንዴ አገልግሎት ይሰጣል። በአጠቃላይ በአንድ ጉዞ 300 ተሳፋሪዎችን በሚይዘው ባቡር ተሳፋሪዎች አንደኛ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ወንበር መምረጥ ይችላሉ። ባቡሩ የመመገቢያ ፍርጎ እና የተለየ የሻንጣ መጓጓዣም አለው። አገልግሎቱ እ.አ.አ በ1995 በፀጥታ ችግር ተቋርጦ የነበረ ሲሆን በ2003 በቴክኒክ ችግር በድጋሚ ቆሟል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0