ኒጀር ውስጥ በጣለ ከባድ ዝናብ 100 የሚሆኑ ሰዎች መሞታቸውን መንግሥት አስታወቀ

ሰብስክራይብ
ኒጀር ውስጥ በጣለ ከባድ ዝናብ 100 የሚሆኑ ሰዎች መሞታቸውን መንግሥት አስታወቀ በግንቦት ወር ከጀመረው የዝናብ ወቅት አንስቶ በሚጥለው ከባድ ዝናብ በትንሹ 94 ሰዎች እንደሞቱ፣ 93 የሚሆኑት ላይ ጉዳት እንደደረሰ እና 137,156 ሰዎች ላይ ችግር እንደተፈጠረ የሰብዓዊ ጉዳዮች እና የአደጋ አስተዳደር ሚኒስትር አይሳ ላኦዋን ዋንዳራማ ሐሙስ ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። በመግለጫው መሰረት 44 ሰዎች በጎርፍ አደጋ ሲሞቱ 50 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በመኖሪያ ቤቶች መደርመስ ህይወታቸውን አጥተዋል። እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ የጎርፍ አደጋው 692 መንደሮችን፣ 129 ወረዳዎችን እና 46 አውራጃዎችን ጨምሮ ስምንቱንም የሀገሪቱን ክልሎች ነክቷል። የምግብ አቅርቦት እየተሰራጨ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች እየተጓጓዙ ይገኛሉ። በተጨማሪም መንግሥት በጎርፍ ለተጎዱ ሰዎች እርዳታ ለማድረስ አስፈላጊ እርምጃዎችን ወስዷል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0