የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የኢኮኖሚ ለውጥ ማነቃቂያ እንደሚሆን የህንድ ባለሃብት ተናገሩ

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የኢኮኖሚ ለውጥ ማነቃቂያ እንደሚሆን የህንድ ባለሃብት ተናገሩ የኢትዮጵያ ብረታብረት ኃ.የተ.የግ.ማ. ዋና ስራ አስፈጻሚ ባሄቬሽ ቻንዳሪያ የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ የተቀዛቀዘውን ኢኮኖሚ በአዎንታዊው ይቀይራል ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል። ለዓመታት ስራ ላይ የቆየው ገዳቢ የቁጥጥር ፖሊሲ ለኢትዮጵያ የሚፈለገውን ውጤት አላስገኘም ብለዋል። ማሻሻያው ስር ነቀል እና ሁሉን አቀፍ እንደሆነ የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚው የውጭ ምንዛሪ መዛባት እና አለመመጣጠንን የመሳሰሉ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን እንደሚቀርፍ አስረድተዋል። "ይህ ማሻሻያ ስር ነቀል ነው። ውጪ ያሉ ጓደኞቼ እና ባለሀብቶች ምን ዓይነት ውጤት ይዞ እንደሚመጣ ለማወቅ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ እየደወሉ ነው። አኔ ሁሉን አቀፍ፣ ሰፊ እና ቢዝነስን ግምት ውስጥ ያስገባ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ኮርፖሬቶች ከዚህ በላይ ሊጠይቁ አይችሉም” ሲሉ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። ባለሀብቱ ማሻሻያው ለሸማቾች ከፍተኛ ወጪ፣ የአማራጭ ውስንነት እና ረጅም የጥበቃ ጊዜ ከፈጠረው ሻጭ ኢኮኖሚ ወደ ውጤታማ እና ፍትሃዊ የግብይት ኢኮኖሚ የሚያሸጋግር ወሳኝ እርምጃ ነው ብለዋል። "አንድ ሶስተኛ የሚሆነው የድሆች ወጪ ተሸፍኗል። መንግሥት ጭማሪውን የሚወስን እና የሚቆጣጠር ይሆናል። በማሻሻያው ነዳጅ፣ ማዳበሪያ፣ የምግብ ዘይት እና የምግብ እቃዎች በዓለም አቀፍ ኤጀንሲዎች እና መንግሥት በኩል ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተካቷል" ብለዋል። "ኢትዮጵያ አሁን የሚያስፈልጋት ተስፈኝነት ነው። ከመገናኛ ብዙሃን፣ ከአሳቢዎች፣ ከነጋዴዎች፣ ከሰራተኛ ማህበራት፣ ከባለሙያዎች እና እንደኛ ካሉ ባለሀብቶች ተስፈኝነት ያስፈልጋል" ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0