የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአህጉሪቱ ማእከል መሆኑን ያጠናክራል የተባለ "ከአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ ነው"ከዋና ከተማው አዲስ አበባ ወጣ ብሎ ቢሾፍቱ አቅራቢያ ለሚገነባው አዲስ ባለ አራት ማኮብኮቢያ የዲዛይን ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ትልቁ አየር ማረፊያ ባለቤት ልትሆን ነው። እ.አ.አ. በ2018 ይፋ የሆነው ይህ ትልቅ ፕሮጀክት በ2029 ወደ ስራ ይገባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በሚኖረው በዓመት 100 ሚልየን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም አሁን ያሉ ሁሉንም የአፍሪካ አየር ማረፊያዎች የሚበልጥ ይሆናል። አዲሱ የአውሮፕላን ማረፊያ ለ270 አውሮፕላኖች ማቆሚያ ቦታም ይኖረዋል። "ይህ የአምስት ዓመት ፕሮጀክት በአፍሪካ ትልቁ ነው" ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል። "በመጀመሪያው የግንባታ ክፍል ብቻ ቢያንስ 6 ቢልየን ዶላር ወጪ ይደረግበታል...ገንዘቡ በብድር የሚሸፈን ሲሆን ፍላጎት ያሳዩ ኩባንያዎች አሉ" ብለዋል። ዱባይ መቀመጫውን ያደረገው የምህንድስና ኩባንያ ሲዳራ የዲዛይን ሂደቱን ይመራል። ማስፋፊያው የኢትዮጵያ ዋና ማዕከል ቦሌ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት 25 ሚልየን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅሙ ላይ ሲቃረብ የመጣ ነው። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአህጉሪቱ ማእከል መሆኑን ያጠናክራል የተባለ "ከአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ ነው"
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአህጉሪቱ ማእከል መሆኑን ያጠናክራል የተባለ "ከአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ ነው"
Sputnik አፍሪካ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአህጉሪቱ ማእከል መሆኑን ያጠናክራል የተባለ "ከአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ ነው"ከዋና ከተማው አዲስ አበባ ወጣ ብሎ ቢሾፍቱ አቅራቢያ ለሚገነባው አዲስ ባለ አራት ማኮብኮቢያ የዲዛይን ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ... 10.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-10T14:35+0300
2024-08-10T14:35+0300
2024-08-10T15:23+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአህጉሪቱ ማእከል መሆኑን ያጠናክራል የተባለ "ከአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ ነው"
14:35 10.08.2024 (የተሻሻለ: 15:23 10.08.2024)
ሰብስክራይብ