እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ ከተማ አል-ዳራጅ ሰፈር በሚገኝ ትምህርት ቤት ባካሄደችው የቦምብ ጥቃት ቢያንስ 100 ሰዎች ሲሞቱ በደርዘን የሚቆጠሩ ቆስለዋል ሲል ፕረስ ቲቪ ዛሬ ቅዳሜ ዘግቧል።

ሰብስክራይብ
እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ ከተማ አል-ዳራጅ ሰፈር በሚገኝ ትምህርት ቤት ባካሄደችው የቦምብ ጥቃት ቢያንስ 100 ሰዎች ሲሞቱ በደርዘን የሚቆጠሩ ቆስለዋል ሲል ፕረስ ቲቪ ዛሬ ቅዳሜ ዘግቧል። የእስራኤል መከላከያ ሃይል (አይ.ዲ.ኤፍ) ጋዛ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት የአየር ድብደባ መፈፀሙን አረጋግጦ የፍልስጤም ንቅናቄ ሃማስ ተዋጊዎች ተጠልለውበት ነበር ብሏል። የእስራኤል መከላከያ ሃይል ከጥቃቱ በፊት “አልሞ ተኳሽ መሳርያዎችን መጠቀም፣ የአየር ላይ ክትትል እና የስለላ መረጃን ጨምሮ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ በርካታ እርምጃዎች ተወስደዋል” ብሏል። ፎቶ እና ተንቀሳቃሽ ምስሉ ከማህበራዊ ትስስር ገፆች የተገኙ ናቸው።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0