የናሚቢያ ሕግ አስከባሪ መኮንኖች በሩሲያ ከፍተኛ የስልጠና ኮርሶችን ወሰዱ

ሰብስክራይብ
የናሚቢያ ሕግ አስከባሪ መኮንኖች በሩሲያ ከፍተኛ የስልጠና ኮርሶችን ወሰዱ ከተለያዩ የናሚቢያ ኤጀንሲዎች የተውጣጡ ተወካዮች ከሰኔ 10 እስከ ሐምሌ 24 ድረስ ስልጠናውን እንደወሰዱ በናሚቢያ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ አስታውቋል።ለተሳታፊዎቹ ሶስት የስልጠና ፕሮግራሞች ተዘጋጅተው እንደነበር ተገልጿል። ከናሚቢያ የመጡት ሰልጣኞች በሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትምህርቶችን ለመውሰድ እድሉን አግኝተዋል፦ 🟠 የውስጥ ጉዳዮች አካላት/ፖሊስ አስተዳደር አደረጃጀት። 🟠 የዘመናዊ ኤክስፐርት ምርመራ እና ልየታ። 🟠 በፊሺንግ፣ ሶሻል ኢንጂነሪንግ እና በሌሎችም መንገዶች የሚፈጸሙ የፋይናንስ ስርቆት ወንጀሎችን መፍታት። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0