በእስራኤል እና ሃማስ መካከል አዲስ ዙር ድርድር ነሐሴ 9 ሊካሄድ እንደሚችል ተገለጸ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ኳታር እና ግብፅ በጋራ ባወጡት መግለጫ መሰረት በእስራኤል እና ሃማስ መካከል አስቸኳይ ድርድር በዶሃ ወይም ካይሮ ይካሄዳል። በሶስቱ ሀገራት መሪዎች የተፈረመው ሰነድ "ቀሪ ክፍተቶችን በሙሉ" ማጥበብ እና በጋዛ ያለ "ተጨማሪ መዘግየት" የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሃሳብ አቅርቧል። ዩናይትድ ስቴትስ፣ ኳታር እና ግብፅ "የመዋቅራዊ ስምምነት ላይ ለመድረስ ለወራት ሲሰሩ ቆይተው ተግባራዊ ዝርዝሮች ብቻ ቀርተውት ጠረጴዛ ላይ ቀርቧል" ሲል ገልጿል መግለጫው። ሀገራቱ "ለረጅም ጊዜ በስቃይ ለነበሩት የጋዛ ህዝቦች እንዲሁም ለረጅም ጊዜ ታግተው ለነበሩት እና ቤተሰቦቻቸው አፋጣኝ እፎይታ ለማምጣት ጊዜው አሁን ነው" ብለዋል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ፅህፈት ቤት ነሐሴ 9 በሚደረገው ድርድር ላይ ለመገኘት የልዑካን ቡድን ለመላክ ዝግጁ እንደሆኑ ያስታወቁ ሲሆን ሃማስ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በእስራኤል እና ሃማስ መካከል አዲስ ዙር ድርድር ነሐሴ 9 ሊካሄድ እንደሚችል ተገለጸ
በእስራኤል እና ሃማስ መካከል አዲስ ዙር ድርድር ነሐሴ 9 ሊካሄድ እንደሚችል ተገለጸ
Sputnik አፍሪካ
በእስራኤል እና ሃማስ መካከል አዲስ ዙር ድርድር ነሐሴ 9 ሊካሄድ እንደሚችል ተገለጸ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ኳታር እና ግብፅ በጋራ ባወጡት መግለጫ መሰረት በእስራኤል እና ሃማስ መካከል አስቸኳይ ድርድር በዶሃ ወይም ካይሮ ይካሄዳል። በሶስቱ ሀገራት መሪዎች... 09.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-09T15:05+0300
2024-08-09T15:05+0300
2024-08-09T15:46+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በእስራኤል እና ሃማስ መካከል አዲስ ዙር ድርድር ነሐሴ 9 ሊካሄድ እንደሚችል ተገለጸ
15:05 09.08.2024 (የተሻሻለ: 15:46 09.08.2024)
ሰብስክራይብ