ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከኪዬቭ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ያቋረጡትን ማሊ እና ኒጀርን በቅርብ እየተከታተለች እንደሆነ ገለጸች

ሰብስክራይብ
ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከኪዬቭ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ያቋረጡትን ማሊ እና ኒጀርን በቅርብ እየተከታተለች እንደሆነ ገለጸች "ዩክሬን ለአሸባሪ ቡድኖች የምታደርገውን ድጋፍ የተመለከተው መረጃ እውነት ሆኖ ከተገኘ በጣም ያሳዝናል ምክንያቱም የማሊ ህዝብ ብዙ ስቃይ ደርሶበታል" ሲሉ የማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ማክሲም ባላው ለስፑትኒክ ተናግረዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የማሊ ህዝብ ነፃነቱን ለማግኘት እና ሉዓላዊነቱን ለማስጠበቅ የሚያደርገውን ጥረት ትደግፋለች። ማሊ ኪዬቭ በአካባቢው አሸባሪዎችን ትደግፋለች በማለት ከዩክሬን ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሰኞ እለት አቋርጣለች። ኒጀር እንዲሁ ከኪዬቭ ጋር የነበራትን ግንኙነት እንዳቋረጠች እሮብ እለት አስታውቃለች። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0