በእንግሊዝ ከተሞች እየደረሰ ያለውን የዘረኝነት ጥቃት ተከትሎ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ለዜጎቻቸው የጉዞ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል

ሰብስክራይብ
በእንግሊዝ ከተሞች እየደረሰ ያለውን የዘረኝነት ጥቃት ተከትሎ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ለዜጎቻቸው የጉዞ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋልበተለያዩ የብሪታንያ ከተሞች በሚገኙ ስደተኞች ላይ ያነጣጠረውን የሃይል እርምጃ ተከትሎ፣ ታንዛኒያውያን ፣ ናይጄሪያውያን እና በእንግሊዝ የሚኖሩ ኬንያውያን አደጋ ላይ ሊጥላቸው ከሚችሉ አካባቢዎች ከመገኘት እንዲቆጠቡ፤ ለደህንነታቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና አንደ አስፈላጊነቱ ከኤምባሲዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት እርዳታ ማግኘት እንዲችሉ ተመክረዋል።"እዚህ እንግሊዝ ያሉ ዜጐች ከእነዚህ አካባቢዎች እንዲርቁ እንመክራለን፤ ከተቻለ ከከፍተኛ ኮሚሽኑ እርዳታ ይጠይቁ " ሲሉ በእንግሊዝ የታንዛኒያ ከፍተኛ ኮሚሽነር ምበልዋ ካይሩኪ ተናግረዋል።በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በተሰራጨው የተሳሳተ መረጃ የተቀሰቀሰው ብጥብጥ፣ በሳውዝፖርት ለሞቱት ሶስት ወጣት ልጃገረዶች፤ ሙስሊም ስደተኞችን በሀሰት በመወንጀል ተጠያቂ አድርገዋል። ወንጀሉን ፈጽሟል የተባለው የ17 ዓመቱ አክሴል ሙጋንዋ ሩዳኩባና ስደተኛ ሳይሆን ስደተኛ ነው በሚል የተነዛው የሀሰት መረጃ እንደሆነም ተገልጿል።የተቃውሞ ሰልፎቹ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ መስጊዶች እና ሆቴሎችን ዒላማ ያደርጉ ሲሆን፤ የፖሊስ ባለስልጣናት ከሁከቱ ጋር ሊተባበሩ እንደሚችሉ በመለየት ሁኔታውን ለመቋቋም ከ6,000 በላይ መኮንኖችን ተሰማርተዋል። ከብጥብጡ ጋር በተያያዘ እስካሁን ከ400 በላይ ሰዎች ታስረዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0