የቱኒዚያ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱ በውሃ እጥረት እና በምርጫ ውጥረት ውስጥ ብትሆንም ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን ከስልጣን አባርረዋል ፕሬዝዳንት ካይስ ሳኢድ አሕመድ ሃቻኒን ትላንት እሮብ አመሻሽ ላይ በማሰናበት የማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትን ካሜል ማዱሪን ተተኪ አድርገው ሾመዋል።እ.አ.አ ነሀሴ 2022 ጀምሮ በስልጣን ላይ የነበሩት ሃቻኒ፣ የምግብ እና የሃይል አቅርቦትን ማረጋገጥን ጨምሮ አለም አቀፍ ችግሮች ቢያጋጥሙትም መንግስታቸው እድገት ማስመዝገቡን ተናግረዋል። በመላ ሀገሪቱ በተከሰተው የውሃ እጥረት እና የመብራት መቆራረጥ ህዝቡ ቅሬታ ማሰማቱን ተከትሎ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ከኃላፊነታቸው እንዲባረሩ መንስኤ የሆነው። መንግስት የመጠጥ ውሃ በሬሽን እስከማከፋፈል ያደረሰው በሀገሪቱ የተከሰተው ከፍተኛ ድርቅ እንደሆነ ቢገልጽም፤ ሰኢድ ግን ግድቦቹ ሙሉ መሆናቸውን በመግለጽ ከመጪው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት የተቀነባበረ ሴራ መሆኑን ይጠቁማሉ።የግብርና ሚኒስቴር በበኩል በግድቦቹ ውስጥ ያለው የውሃ መጠን እጅግ በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ይህም፤ የግድቡ የውሃ መጠን 25 በመቶ ብቻ መሆኑን አስታውቋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የቱኒዚያ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱ በውሃ እጥረት እና በምርጫ ውጥረት ውስጥ ብትሆንም ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን ከስልጣን አባርረዋል
የቱኒዚያ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱ በውሃ እጥረት እና በምርጫ ውጥረት ውስጥ ብትሆንም ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን ከስልጣን አባርረዋል
Sputnik አፍሪካ
የቱኒዚያ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱ በውሃ እጥረት እና በምርጫ ውጥረት ውስጥ ብትሆንም ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን ከስልጣን አባርረዋል ፕሬዝዳንት ካይስ ሳኢድ አሕመድ ሃቻኒን ትላንት እሮብ አመሻሽ ላይ በማሰናበት የማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትን ካሜል ማዱሪን... 08.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-08T13:03+0300
2024-08-08T13:03+0300
2024-08-08T13:46+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የቱኒዚያ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱ በውሃ እጥረት እና በምርጫ ውጥረት ውስጥ ብትሆንም ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን ከስልጣን አባርረዋል
13:03 08.08.2024 (የተሻሻለ: 13:46 08.08.2024)
ሰብስክራይብ