ሳይንቲስቶች በግብፅ 63 መቃብሮችን ማግኘታቸው ሲገለጽ ይህም "የጥንታዊ ስልጣኔን ምስጢር" የሚገልጥ እንደሆነ ተጠቁሟል

ሰብስክራይብ
ሳይንቲስቶች በግብፅ 63 መቃብሮችን ማግኘታቸው ሲገለጽ  ይህም "የጥንታዊ ስልጣኔን ምስጢር" የሚገልጥ እንደሆነ ተጠቁሟልበዳሚታ በተካሄደው ቁፋሮ የኮትብ ፋውዚ የአርኪኦሎጂ ቡድን ከ2,500 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩ መቃብሮችን፤ ከወርቅ የተሠሩ ቅርሶችን፣ ሳንቲሞችንእና የሸክላ ዕቃዎችን አግኝተዋል። የግብፅ የቱሪዝም እና የጥንት ቅርሶች ሚኒስቴር እንደገለጸው እነዚህ ግኝቶች በጊዜው የነበሩትን የቀብር ልማዶች ጨምሮ "የጥንቱን የግብፅ ስልጣኔ ምስጢር" ለመግለጥ ይረዳሉ ብሏል።ታል አል-ዲር በመባል የሚታወቀው ቦታ ኔክሮፖሊስ ነው። የመቃብር ስፍራው በተለይ በ26ኛው ሥርወ መንግሥት ዘመን በጣም አስፈላጊ የነበረ እና በባይዛንታይን ዘመናት በሙሉ ጥቅም ይውል እንደነበር ተገልጿል። በታል ኤል-ዲር አርኪኦሎጂስቶች ከፍተኛ ማህበራዊ ደረጃ የነበራቸው ሰዎች የተቀበሩበት ትልቅ መቃብር አግኝተዋል። ከአስከሬኖቹ ቀጥሎ ሃይማኖታዊ ምልክቶችን እና ጥንታዊ የግብፃውያን ጣዖታትን የሚመስሉ የወርቅ ጥቅሎች አብረው እንደተገኙ ተገልጿል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0