የነሐሴ 1 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎችን

ሰብስክራይብ
የነሐሴ 1 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎችን ቭላድሚር ፑቲን በኩርስክ ስላለው ሁኔታ ከመንግስት እና ከፀጥታ ሀይሎች ጋር ውይይት አድርገዋል። ፕሬዚዳንቱ የኪየቭ አገዛዝ ድርጊት መጠነ ሰፊ ትንኮሳ ነው ብለውታል። ኢታማዦር ሹም ቫለሪ ገራሲሞቭ እንደገለጹት በክልሉ በዩክሬን ወታደሮች ላይ በደረሰው ጉዳት 315 ወታደሮች ሲሞቱ፤ 54 የጦር ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን ተናግረዋል። ወደ ሩሲያ ግዛት የሚያደረጉት ግስጋሴም ተገትቷል። ዩናይትድ ስቴትስ በኩርስክ ክልል ስላለው የዩክሬን ጦር ሃይል ሁኔታ ኪየቭ መረጃ እንድትሰጣት እየጠየቀች መሆኑን ዋይት ሀውስ አስታውቋል። ዘለንስኪ በዩክሬን የማርሻል ህግን እና አጠቃላይ እንቅስቃሴን እስከ ህዳር 9 ድረስ የሚያራዝሙ ህጎችን ፈርመዋል። የባንግላዲሽ ጊዜያዊ መንግስትን እንዲመሩ የተሰየሙት የኖቤል ተሸላሚው ሙሀመድ ዩኑስ አሁን ካላቸው ስልጣን ውጪ፤ በቋሚነት የሕዝብ ተመራጭ ሆኖ የመቀጠል ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል። የሃማስ ፖሊት ቢሮ ሃላፊ ኢስማኢል ሃኒዬህ በተኙበት ሞተው በፈራረሱ ግድግዳዎች ስር እንደተተገኙ የኢራን የዓይን እማኝ እና የንቅናቄው ተወካይ ካሊድ ካዱሚ ለስፑትኒክ ተናግሯል። በማህበራዊ ሚዲያ ከስደተኞች ጋር ሆቴሎችን ለማቃጠል ሲያነሳሳ የነበረው ባለስልጣን ሚስት በእንግሊዝ መያዟን የምዕራቡ አለም መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0