ዚምባብዌ በዶላር የሚደረግ ግብይትን ለማቆም የሚያስችላትን ፍኖተ ካርታ ይፋ ልታደረግ ነው

ሰብስክራይብ
ዚምባብዌ በዶላር የሚደረግ ግብይትን ለማቆም የሚያስችላትን ፍኖተ ካርታ ይፋ ልታደረግ ነውየዚምባብዌ በቡሊዮን (ወርቅ) የሚደገፈውን ዚግ የተሰኘውን ገንዘቧን በኢኮኖሚው ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማዋሃድ እየስራች ነው ሲሉ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ጄንፋን ሙስዌ ከካቢኔ ስብሰባ በኋላ በሰጡት መግለጫ ወቅት ተናግረዋል።የእንቅስቃሴው አላማ የዚምባብዌን በዶላር ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ ሲሆን፤ ዶላር በአሁኑ ጊዜ ከሁሉም የኢኮኖሚ ግብይቶች ውስጥ 70 በመቶውን ይይዛል። ከመጀመሪያው 2030 ቀነ ገደብ አስቀድሞ፤ ሀገሪቱ በ2026 ዚግ ብቸኛ መገበያያ ገንዘብ እንዲሆን ለማድረግ አቅዳለች።የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ኢመርሰን ምናንጋግዋ በሰኔ ወር በሴንት ፒተርስበርግ የኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባ ወቅት ለስፑትኒክ እንደተናሩት፤ በዶላር ያልተደገፈውን ዚጊን ከማስተዋወቅ በፊት የወርቅ ክምችቶችን ለማሳደግ ሁለት አመታትን እንደፈጅባቸው መናገራቸው ይታወሳል።"ገንዘባችን ጠንካራ መሠረት እንዲኖረው ማድረግ እንደሚገባ ይሰማናል። ይህም ባለን ጠንካራ የወርቅ ክምችት ላይ እንዲመሠረት ማድረግ ነው፤ ይህንኑ ነው ያደረግነው" ሲሉ ሙስዌ አብራርቷል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0