የሐምሌ 30 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች በባንግላዲሽ በተፈጠረው ግጭት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 109 መድረሱን ፖሊስ እና የህክምና ምንጮችን ጠቅሶ ኤኤፍፒ ዘግቧል። ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት ለመሰንዘር በዝግጅት ላይ ስትሆን በሚሳኤል ማስወንጨፊያዎች ጥቃቱን ልታደርስ እንደምትችል ጠቁመው፤ አሜሪካ ቴህራን ግጭቱን እንዳታባባስ ጠይቃለች ሲል ዎል ስትሪት ጆርናል ዘግቧል። የዩክሬን ጦር ሃይሎች በቤልጎሮድ ክልል አንድ ተሽከርካሪ ላይ ባደረሱት ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የቤልጎሮድ ገዥ አስታውቀዋል። በኩርስክ ክልል ደግሞ በመኪና ላይ በደረሰ ጥቃት ሁለት ሰዎች ወቁስላቸውን ተጠባባቂው አስተዳዳሪው ተናግረዋል። የዩክሬን ጦር ሃይሎች የኩርስክ ክልልን ግዛት ለማፍረስ ቢሞክሩም የኤፍኤስቢ ድንበር አገልግሎት ተዋጊዎች እና የሩሲያ ጦር ሃይሎች ወረራውን መከላከል ችለዋል ሲሉ ተጠባባቂው አስተዳዳሪ አስታውቀዋል።በኢራቅ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮችን ያስተናገደው የአየር ኃይል ማረፊያ በተከፈተ ተኩስ በርካታ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ ጉዳት መድረሱን ፔንታጎን ገልጿል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሐምሌ 30 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
የሐምሌ 30 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
Sputnik አፍሪካ
የሐምሌ 30 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች በባንግላዲሽ በተፈጠረው ግጭት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 109 መድረሱን ፖሊስ እና የህክምና ምንጮችን ጠቅሶ ኤኤፍፒ ዘግቧል። ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት ለመሰንዘር በዝግጅት ላይ ስትሆን በሚሳኤል ማስወንጨፊያዎች... 06.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-06T11:31+0300
2024-08-06T11:31+0300
2024-08-06T12:23+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий