የሐምሌ 29 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች የዩክሬን ጦር ሃይሎች በቤልጎሮድ ክልል ቭያዞቮዬ መንደር በሚገኝ የግብርና ድርጅት አውቶብስ ላይ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ባደረሱት ጥቃት አንድ ሰው ሲሞት 3 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የአካባቢው ገዥ ተናግረዋል። የአሜሪካ ወታደራዊ መኮንኖች በሰሜናዊ ኒጀር አጋዴዝ ከተማ የሚገኘውን የአየር ጦር ሰፈር ለቀው መውጣታቸውን የሁለቱም ሀገራት ጦር ሃይሎች በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። እ.አ.አ በሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ የአሜሪካ ጦር በዋና ከተማይቱ ኒያሚ የሚገኘውን ጦር ሰፈር መልቀቁ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ወደ 200 የሚጠጉ የአሜሪካ ወታደሮች በአጋዴዝ ቀርተው ነበረ። ስልጣን የለቀቁት የባንግላዲሽ ጠቅላይ ሚንስትር በእንግሊዝ ጥገኝነት የጠየቁ ሲሆኑ እህታቸው ቀድም ብለው የእንግሊዝ ዜግነት መያዛቸው ተገልጿል። በባንግላዲሽ በተነሳው ሁከት ሳቢያ በዛሬው ዕለት ብቻ ቢያንስ 56 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። የስዊዘርላንድ ወታደራዊ ፍርድ ቤት በዩክሬን ውስጥ በቅጥረኝነት ተግባር የተጠረጠሩ የስዊዘርላንድ ዜጎች ላይ 13 የምርመራ መዝገቦችን መክፈታቸው ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ባይደን እና ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ የአክሲዮን ገበያው እንዲወድቅ አድርገዋል ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ ከሰዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሐምሌ 29 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
የሐምሌ 29 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
Sputnik አፍሪካ
የሐምሌ 29 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች የዩክሬን ጦር ሃይሎች በቤልጎሮድ ክልል ቭያዞቮዬ መንደር በሚገኝ የግብርና ድርጅት አውቶብስ ላይ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ባደረሱት ጥቃት አንድ ሰው ሲሞት 3 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የአካባቢው ገዥ... 05.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-05T20:24+0300
2024-08-05T20:24+0300
2024-08-05T21:46+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий