“ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የጋራ መግባባት” ፡ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ስላለው አሁናዊ እና የወደፊት ሁኔታ ላይ የተነገሩት

ሰብስክራይብ
“ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የጋራ መግባባት” ፡ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ስላለው አሁናዊ እና የወደፊት ሁኔታ ላይ የተነገሩትእ.ኤ.አ. በ2019 እና በ2023 የሁለቱም ሀገራት መሪዎች በሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ከተገናኙ በኋላ የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን ኢቭጊኒ ተሬኪን ከመንግስት ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል። “ ትብብሩ የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸው፤ በተለይም በሃይል፣ በጋራ ንግድ፣ በምግብ ዋስትና እና በሌሎችም መስኮች ጎለተው እንደሚታዩ ተናግረዋል።ተሬኪን ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ እየተካሄደ ያለውን ጥረት በማንሳት፤ ኢኮኖሚያዊ አጋርነት ላይ ይበልጥ ተስፋ ሰንቋል። ከዚህም በላይ ሁለቱም ሀገራት በአለም አቀፍ ህግ የሚመራ እና በተባበሩት መንግስታት ቻርተር ውስጥ በተገለጹት እሴቶች የሚ የሚያከብር ብዙኀ አለምአቀፍ ስርዓት ማንበር ላይ ተመሳሳይ አመለካከት አላቸው። ዲፕሎማቱ በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ ሀገራትን መስተጋብር አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን፤ የብሪክስ ህብረት የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማስፋት እና ለማጠናከር የተሻሉ እድሎችን እንደሚፈጥር ገልፀው አሁን ላይ ያሉ ጉልህ እና የተሳሰሩ ሀሳቦችን እና ወሳኝ የፖለቲካ ግስጋሴውን አንስተዋል። በመጨረሻም ሩሲያ ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በየዓመቱ የምታደርገውን የስኮላርሺፕ እድል እና የህዝብ ለህዝብ ትብብርና ግንኙነትን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0