የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፀሐፊ ሰርጌ ሾጉ ከኢራን ከፍተኛ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፀሀፊ አሊ አክባር አህመዲያን ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ሰብስክራይብ
የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፀሐፊ ሰርጌ ሾጉ ከኢራን ከፍተኛ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፀሀፊ አሊ አክባር አህመዲያን ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። ሾይጉ በአለም አቀፍ እና በቀጠናዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኢራን መግባታቸውን የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት በዛሬው እለት አስታውቋል።ሾይጉ ከኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ጋር እንዲሁም ከኢራን ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም መሀመድ ባገሪ ጋርም እንደሚወያዩ ተነግሯል።አጀንዳው በቴህራን እና በሩሲያ መካከል የሚኖረውን የደህንነት እና የኢኮኖሚ ጉዳዮችን ​​ጨምሮ በሌሎች በርካታ የትብብር ጉዳዮችን እንደሚያጠቃል ተገልጿል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0