በባንግላዲሽ በፖሊስ እና በተቃዋሚዎች መካከል በተነሳ ግጭት በአንድ ቀን ከ90 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ

ሰብስክራይብ
በባንግላዲሽ በፖሊስ እና በተቃዋሚዎች መካከል በተነሳ ግጭት በአንድ ቀን ከ90 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተዘገበበፀረ-መንግስት ተቃውሞ የፖሊስ መኮንኖችን ጨምሮ በአጠቃላይ ቢያንስ 300 ሰዎች ሞተዋል።እ.ኤ.አ ነሐሴ 4 በዋና ከተማይቱ ዳካ እና በሌሎች የሪፐብሊኩ ከተሞች በተቃዋሚዎች እና በመንግስት ደጋፊዎች መካከል አዲስ ግጭት ተቀስቅሷል። ተቃዋሚዎቹ የባንግላዲሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሃሲና ስልጣን እንዲለቁ እየጠየቁ ነው።በሀምሌ ወር መጀመሪያ በደቡብ እስያዊቷ ሀገር በሚገኙ ተማሪዎች በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ እያደረጉ ነው። የተቃውሞ ሰልፉ መነሻ በ1971 በተደረገው የነፃነት ጦርነት ላይ ተሳታፊ ለነበሩ ሰዎች ዘመዶች የሚሰጠውን የስራ ኮታ አሰራርን በመቃወም የተጀመረ ነበር። የተቃውሞ ሰልፉ ቀስ በቀስ እየተባባሰ ሄዶ ሰልፉ ወደ ግጭት ሊቀየር ችሏል።ቪዲዮ ከማህበራዊ መገናኛ አውታረ መረቦች የተገኘ ነውስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0