ኢብራሂም ትራኦሬ ቡርኪናፋሶን "ከክፉ ኃይሎች እና ደጋፊዎቻቸው" ነፃ ለማውጣት ቃል ገቡ

ሰብስክራይብ
ኢብራሂም ትራኦሬ ቡርኪናፋሶን "ከክፉ ኃይሎች እና ደጋፊዎቻቸው" ነፃ ለማውጣት ቃል ገቡ ቡርኪናፋሶ እ.አ.አ. በ1980ዎቹ በካፒቴን ቶማስ ሳንካራ የታወጀውን ትግል እየዘከረች ባለችበት ወቅት የሀገሪቱ መሪ እሁድ እለት በጻፉት መልእክት የተናገሩት ነው። "ትውስታው ለወደፊት እርምጃችን አነቃቂ እና ለምናከናውነው ተግባራት ብርታት የሆነውን የሀገሪቱን ጀግና ስንዘክር ቡርኪናፋሶን ከክፉ ኃይሎች እና ደጋፊዎቻቸው ነፃ ለማውጣት እና ለሁሉም ቡርኪናቤ ተሰፋ የሆነች መሬት ለማድረግ ያለኝን ጽኑ አቋም እና ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጣለሁ" ሲሉ ትራኦሬ ጽፈዋል። እ.አ.አ. ነሐሴ 4 ቀን 1984 ቶማስ ሳንካራ የሀገሪቱን ስም ከአፐር ቮልታ ወደ ቡርኪናፋሶ በመቀየር አዲስ ብሔራዊ መዝሙር እና ባንዲራ አስተዋውቋል። ሳንካራ ሙስናን ለመዋጋት፣ ራስን መቻል ለማበረታታት፣ የሴቶችን መብት ለማስከበር፣ ጤና እና ትምህርትን ለማጠናከር ዋና ዋና የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የአካባቢ ጥበቃ ማሻሻያዎችን ስራ ላይ አውሏል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0