ሄዝቦላ በሰሜን እስራኤል "በደርዘን የሚቆጠሩ" ሮኬቶችን አስወነጨፈ "የእስልምና የተቃውሞ እንቅስቃሴ (ሄዝቦላ) አዲሱን የቤይት ሂሌል ሰፈራን በጥቃቱ ውስጥ ያካተተ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በደርዘን የሚቆጠሩ ካትዩሻ ሮኬቶችን ሰፈራው ላይ ተኩሷል" ሲል የሊባኖሱ ቡድን በመግለጫው አስታውቋል። ሄዝቦላ ጥቃቱን የፈፀመው በደቡባዊ ሊባኖስ በሚገኙ ሰፈራዎች ላይ የእስራኤል መከላከያ ሃይል ላደርሰው ጥቃት መልስ ለመስጠት እንደሆነ ገልጿል። እስራኤል ለጥቃቱ ምላሽ የአይረን ዶም ሚሳይል መከላከያ ስርአቷን እንዳነቃች የዘገበው ታይምስ ኦፍ እስራኤል በገሊላ ላይ ሮኬቶቹ ሲጨናገፉ ይታይ ነበር ብሏል። የጥቃቱ የመጀመሪያ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የተሰራጩ ሲሆን አይረን ዶሙ ሮኬቶቹን ሲያጨናግፍ ያሳያሉ። ከሰዓታት በፊት የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ክፋርኬላ፣ ዲር ሰርያን እና ኦዳይሴህ በሚገኙ የሄዝቦላ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ማድረሱን አስታውቋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሄዝቦላ በሰሜን እስራኤል "በደርዘን የሚቆጠሩ" ሮኬቶችን አስወነጨፈ
ሄዝቦላ በሰሜን እስራኤል "በደርዘን የሚቆጠሩ" ሮኬቶችን አስወነጨፈ
Sputnik አፍሪካ
ሄዝቦላ በሰሜን እስራኤል "በደርዘን የሚቆጠሩ" ሮኬቶችን አስወነጨፈ "የእስልምና የተቃውሞ እንቅስቃሴ (ሄዝቦላ) አዲሱን የቤይት ሂሌል ሰፈራን በጥቃቱ ውስጥ ያካተተ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በደርዘን የሚቆጠሩ ካትዩሻ ሮኬቶችን ሰፈራው ላይ ተኩሷል" ሲል... 04.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-04T18:29+0300
2024-08-04T18:29+0300
2024-08-04T18:46+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий