የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት በኑሮ ውድነት ምክንያት የተነሳው ተቃውሞ እና “ደም መፋሰሱ” እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ

ሰብስክራይብ
የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት በኑሮ ውድነት ምክንያት የተነሳው ተቃውሞ እና “ደም መፋሰሱ” እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ "ውድ ናይጄሪያውያን በተለይም ወጣቶች ድምፃችሁን በግልጽ ሰምቻለሁ። ለተቃውሞው ግፊት የሆነውን ስቃይ እና ብስጭት ተረድቻለሁ። እናም መንግሥታችን የዜጎቻችንን ችግር ለመስማት እና ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ" ሲሉ ቦላ ቲኑቡ ተናግረዋል። ሁሉም ናይጄሪያውያን "በክብር እና ብልጽግና" የሚኖሩበት ብሩህ ዘመን ለመፍጠር በጋራ መስራት አስፈላጊ መሆኑን በማጉላት ሁከትና ውድመት ሀገሪቱን እንዲከፋፍሉ ከመፍቀድ ሁሉም እንዲቆጠብ አሳስበዋል። 🪧 የተቃውሞ ሰልፎችን ለማዘጋጀት የኦንላይን ፕላትፎርሞችን እየተጠቀሙ ያሉት ናይጄሪያውያን የነዳጅ ዋጋ እና የመብራት ታሪፍ እንዲቀንስ እና ሌሎች ጥያቄዎችንም እያቀረቡ ይገኛሉ። ቲኑቡ በሰጡት ምላሽ የኢኮኖሚ ፖሊሲያቸውን የደገፉ ሲሆን "መንግሥታችን የኢኮኖሚያችንን መሰረት በመገንባት መጪውን ዘመን የበዛ እና የተትረፈረፈ እንዲሆን የሚያስችል ጉልህ እመርታዎችን አሳክቷል" ብለዋል። ሀሙስ እና አርብ በመላ ሀገሪቱ በተካሄደው የሁለት ቀን የተቃውሞ ሰልፍ በአጠቃላይ 681 ሰዎች መታሰራቸውን ፖሊስ በመግለጫው አስታውቋል። ፖሊስ በትጥቅ የታገዘ ዘረፋ፣ ቃጠሎ፣ ሥርዓት አልበኝነት፣ የመንግሥትና የግል ንብረት ማውደምን ጨምሮ የወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል። በተፈጠረው አለመረጋጋት በትንሹ 17 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0