የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራውን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከ27 ቢልዮን ዶላር በላይ ገቢ ሰበሰበች

ሰብስክራይብ
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራውን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከ27 ቢልዮን ዶላር በላይ ገቢ ሰበሰበች ገንዘቡ የተሰበሰበው ከእዳ ስረዛ፣ ከዓለም አቀፍ ዕርዳታ እና ከአጋርነቶች እንደሆነ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝን ጠቅሶ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ፖሊሲው ቀጣይነት ያለው እድገት እና ለዜጎች ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማምጣት ያለመ ነው። በግብርና፣ ማዕድን እና ቱሪዝም ዘርፍ እየተካሄደ ባለው ማሻሻያ ሀገሪቱ ከ30% ወደ 17% የዕዳ ጫናዋን ከማቅለሏ ባለፈ የውጭ ኢንቨስትመንትንና የኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማሳደግ ዝግጁ መሆኗን ዘገባው አመልክቷል። እዮብ ተካልኝ አያይዘውም መንግሥት ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ያለው ቁርጠኝነት ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሸጋገር መንገድ እየጠረገ መሆኑንም ጠቁመዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0