የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት በግጭት ውስጥ የምትታመሰው ዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክን ለማረጋጋት ክልላዊ ትብብር አስፈላጊ እንደሆነ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት በግጭት ውስጥ የምትታመሰው ዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክን ለማረጋጋት ክልላዊ ትብብር አስፈላጊ እንደሆነ ተናገሩ በዛምቢያ አቻቸው ሃካይንዴ ሂቺሌማ ግብዣ በሀገሪቱ የሶስት ቀን ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳዪሺሚዬ በዛምቢያ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር "በተለይ የኤም 23 አማፂያን በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንደገና ማንሰራራቱ ያሳስበኛል" ብለዋል። ንዳዪሺሚዬ ቡሩንዲ ከታንዛኒያ እና ዲአርሲ ጋር የሚያዋስናትን ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ አንስተው ይህም የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳድክ) ወሳኝ አካል እንድትሆን እንደሚያደርጋት ተናግረዋል። "በቀጠናው የሰላም ጥረቶች እንደ ሽብርተኝነት፣ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር እና የስደተኞች ቁጥር መጨመርን የመሳሰሉ ስጋቶችን ለመፍታ የበኩላችንን አስተዋፅኦ ለማበርከት ቡሩንዲ የሳድክ አባል የመሆን ፍላጎት አላት" ያሉት ፕሬዝዳንቱ ቡሩንዲ እና ዛምቢያ በዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ ሰላም ለማስፈን የሚያደርጉትን ትብብር አድንቀዋል። ፕሬዝዳንት ንዳዪሺሚዬ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ድርቅ ከተመታችው ዛምቢያ ጋር አብሮነታቸውን ለማሳያት 5,000 ቶን ሩዝ፣ ባቄላ እና በቆሎ መለገሳቸውንም አስታውቀዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0