የቻይና፣ ሞዛምቢክ እና ታንዛኒያ መከላከያ ሃይሎች በምስራቅ አፍሪካ የጋራ ልምምድ አካሄዱ

ሰብስክራይብ
የቻይና፣ ሞዛምቢክ እና ታንዛኒያ መከላከያ ሃይሎች በምስራቅ አፍሪካ የጋራ ልምምድ አካሄዱ "የሰላም አንድነት 2024" የባህር እና የምድር ልምምድ በታንዛኒያ ግዛት እና በባህር ዳርቻ ውሃዎቿ ላይ እየተካሄደ መሆኑን የወታደራዊ ዜና ፖርታል ዲፌንስዌብ ዘግቧል። ልምምዱ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ለሚደረገው ወታደራዊ ዘመቻ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥም ህትመቱ አስታውቋል። የባህር ላይ ልምምዱ ሐምሌ 29 የሚጠናቀቅ ሲሆን የምድር ልምምዱ ነሐሴ 5 ያበቃል። የሰላም አንድነት የጋራ ልምምድ በታንዛኒያ እና የቻይና መከላከያ ሃይሎች መካከል ለመጀመሪያ ግዜ እ.አ.አ 2014 ነበር የተደረገው። የጋራ ልምምዱ ለአራተኛ ግዜ እየተካሄደ ሲሆን ከታንዛኒያ ጋር የምትዋሰነው ሞዛምቢክ በልምምዱ ላይ ለመጀመሪያ ግዜ ተሳትፋለች። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0