የጂኦሎጂ አሰሳ በሩሲያ እና ታንዛኒያ መካከል ተስፋ ሰጪ የትብብር መስክ እነደሆነ የሩሲያ አምባሳደር ተናገሩ

ሰብስክራይብ
የጂኦሎጂ አሰሳ በሩሲያ እና ታንዛኒያ መካከል ተስፋ ሰጪ የትብብር መስክ እነደሆነ የሩሲያ አምባሳደር ተናገሩ "ታንዛኒያ ከፍተኛ የኢነርጂ እምቅ አቅም አላት...የሃይል ሃብቱ የውሃ ሃይል፣ ዩራኒየም፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የድንጋይ ከሰል እና የታዳሽ ሃይል ምንጮችን ያካትታል" ሲሉ በታንዛኒያ የሩሲያ አምባሳደር አንድሬ አቬትስያን ከስፑትኒክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። ታንዛኒያ 1.6 ትሪልየን ኪዩቢክ ሜትር የሚደርስ እምቅ ክምችት የያዘውን የጋዝ ኢንዱስትሪ በንቃት በማልማት ላይ ትገኛለች ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በታንዛኒያ ውስጥ በሩሲያ የነዳጅና ጋዝ ኩባንያዎች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የሉም ነገር ግን አፍሪካዊቷ ሀገር ፖሊሲዋን ክፍት ወደማድረግ በመሸጋገሯ ከወዲሁ የዋና ዋና የሩሲያ ኩባንያዎችን ትኩረት እንደሳበ አምባሳደሩ አስታውቀዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0