ዚምባብዌ በሩሲያ ድጋፍ በደቡብ አፍሪካ ክልል የአየር አምቡላንስ ማዕከል ለማቋቋም እንዳቀደች ተገለፀ የዚምባብዌ የጤና ሚኒስትር ዳግላስ ሞምቤሾራ ይህ ተነሳሽነት በክልሉ ውስጥ ወሳኝ የድንገተኛ ህክምና አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ እና በሞስኮ እና ሃራሬ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ የጤና አገልግሎት ትብብር የበለጠ እንደሚያጠናክር ተናግረዋል። ሞምቤሾራ ከሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሀገራቸው በአሁኑ ወቅት በሩሲያ ድጋፍ ለአብራሪዎች እና ህክምና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠትን ጨምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአየር አምቡላንስ አገልግሎት በማቋቋም ላይ ትገኛለች። የሩሲያ ሄሊኮፕተሮች በቅርቡ መገዛታቸውን እና የዚምባብዌ አብራሪዎች በሩሲያ ስፔሻሊስቶች ስልጠና እያገኙ እንደሆነም ጠቁመዋል። ሚኒስትር ሞምቤሾራ ዚምባብዌ ነፃነቷን ከማግኘቷ በፊት ሩሲያ ለዚምባብዌ አብራሪዎች፣ ዶክተሮች እና ለሌሎች ባለሙያዎች ስልጠና ትሰጥ እንደነበር አንስተው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነት አጽንኦት ሰጥተዋል። ሚኒስትሩ ሩሲያ ውስጥ የህክምና ትምህርት የሚያጠኑ የዚምባብዌ ተማሪዎችን ቁጥር መጨመርን ጨምሮ ወደ ፊት ከሩሲያ ጋር የጤና አገልግሎት ትብብርን የማሳደግ ሐሳብ እንዳላቸው አብራተዋል። እንዲሁም የላቀ የሩሲያ የሕክምና እውቀትና ቴክኒኮችን እንዲያዳብሩ ለብቁ ባለሙያዎች አጫጭር ኮርሶችን የመስጠት ሀሳብ አቅርበዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ዚምባብዌ በሩሲያ ድጋፍ በደቡብ አፍሪካ ክልል የአየር አምቡላንስ ማዕከል ለማቋቋም እንዳቀደች ተገለፀ
ዚምባብዌ በሩሲያ ድጋፍ በደቡብ አፍሪካ ክልል የአየር አምቡላንስ ማዕከል ለማቋቋም እንዳቀደች ተገለፀ
Sputnik አፍሪካ
ዚምባብዌ በሩሲያ ድጋፍ በደቡብ አፍሪካ ክልል የአየር አምቡላንስ ማዕከል ለማቋቋም እንዳቀደች ተገለፀ የዚምባብዌ የጤና ሚኒስትር ዳግላስ ሞምቤሾራ ይህ ተነሳሽነት በክልሉ ውስጥ ወሳኝ የድንገተኛ ህክምና አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ እና በሞስኮ እና ሃራሬ... 02.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-02T19:07+0300
2024-08-02T19:07+0300
2024-08-02T19:46+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ዚምባብዌ በሩሲያ ድጋፍ በደቡብ አፍሪካ ክልል የአየር አምቡላንስ ማዕከል ለማቋቋም እንዳቀደች ተገለፀ
19:07 02.08.2024 (የተሻሻለ: 19:46 02.08.2024)
ሰብስክራይብ