የደቡብ አፍሪካ ህዝብ ብዛት በአንድ ዓመት ከ835,500 በላይ ህዝብ ጨምሮ ከ63 ሚልዮን ተሻገረ

ሰብስክራይብ
የደቡብ አፍሪካ ህዝብ ብዛት በአንድ ዓመት ከ835,500 በላይ ህዝብ ጨምሮ ከ63 ሚልዮን ተሻገረ የሀገሪቱ ህዝብ ቁጥር እ.አ.አ ከሐምሌ 2023 እስከ ሐምሌ 2024 የ1.33% ጭማሪ አሳይቶ በ835,513 ሰዎች እንዳደገ እና 63.02 ሚልዮን እንደደረሰ የስታቲስቲክስ ደቡብ አፍሪካ የ2024 የግማሽ ዓመት የህዝብ ቆጠራ መረጃ አመላክቷል። "መረጃው ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች እንደሆኑ እና በአጠቃላይ 32 ሚልዮን መድረሳቸውን አሳይቷል" ሲል ስታቲስቲክስ ደቡብ አፍሪካ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ‍‍‍ የጋውቴንግ ግዛት 16 ሚልዮን የሚጠጋ ህዝብ በመያዝ በሀገሪቱ ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ያለው ክልል ሆኖ ቀጥሏል። ክዋዙሉ-ናታል በ12.3 ሚልዮን ሁለተኛ ነው። ሁለቱ ግዛቶች 45% የሚሆነው የደቡብ አፍሪካ ህዝብ መኖሪያ ናቸው። ሰሜናዊ ኬፕ በ1.4 ሚልዮን በጣም ትንሽ ህዝብ የሚኖርበት ክልል ነው። ስታቲስቲክስ ደቡብ አፍሪካ በተጨማሪም ሀገሪቱ በህክምና፣ በህብረተሰብ ጤና እና በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገቶች ባስመዘገበችው ውጤት ምክንያት የዕድሜ ጣርያ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። "የዕድሜ ጣርያ አሁን 66.5 ዓመት ደርሷል" ያሉት አጥኚዎቹ "ይህም በ2005 ከነበረው 53.6 የዕድሜ ጣርያ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል" ሲሉ ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0