ሩሲያ ለዚምባብዌ የፀረ ኮሌራ መድኃኒት ጥቅል ለገሰች የሰብዓዊ እርዳታ ጭነቱ በዓለም ጤና ድርጅት ትብብር ሃራሬ ደርሷል። ጭነቱ የመድሃኒት ዕቃዎችን፣ የፍጆታ ዕቃዎችን እና የህክምና መሳሪያዎችን እንዳካተተ የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የዚምባብዌ የጤና እና የህጻናት ህክምና ሚኒስትር ዳግላስ ሞምበሾራ ለተደረገው ድጋፍ ለሩሲያ መንግሥት ልባዊ ምስጋናቸውን ገልፀው ድጋፉ ኮሌራን ለመዋጋት ትልቅ አስተዋፅዖ እንዳለው ተናግረዋል። ባለሥልጣኑ አክለውም መድኃኒቶቹ የታመሙትን ለማከም ወሳኝ ናቸው ብለዋል። ሞትን ለመከላከል በጣም አስፈላጊ ወደሆኑባቸው ቦታዎች እንደሚሰራጩም ገለጸዋል። ዚምባብዌ በቅርቡ የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ እንደቆመ ብታስታውቅም የሩሲያ ድጋፍ ሀገሪቱ የሰው ህይወት የማዳን አቅሟን እንድታጠናክር ይረዳታል ሲሉም አክለዋል። በዚምባብዌ እና ሩሲያ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት ሚኒስትሩ ሞስኮ የዚምባብዌን የጤና ዘርፍ ለማሻሻል የህክምና ባለሙያዎችን ማሰልጠን ልትጀምር እንደሆነም አስታውቀዋል። የኮሌራ ወረርሽኝ በተለያዩ የደቡባዊ አፍሪካ ሀገሮች በተለይም ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክ እና ታንዛኒያ በቅርቡ ተከስቷል። በያዝነው ዓመት የካቲት ወር የሳዲክ አባል ሀገራት መሪዎች እና መንግሥት አስቸኳይ ጉባኤ በክልሉ የኮሌራ ክትባት በስፋት ለማከናወን እና በድንበር ላይ የንፅህና ቁጥጥርን ለማጠናከር ወሳኔ አስተላልፏል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሩሲያ ለዚምባብዌ የፀረ ኮሌራ መድኃኒት ጥቅል ለገሰች
ሩሲያ ለዚምባብዌ የፀረ ኮሌራ መድኃኒት ጥቅል ለገሰች
Sputnik አፍሪካ
ሩሲያ ለዚምባብዌ የፀረ ኮሌራ መድኃኒት ጥቅል ለገሰች የሰብዓዊ እርዳታ ጭነቱ በዓለም ጤና ድርጅት ትብብር ሃራሬ ደርሷል። ጭነቱ የመድሃኒት ዕቃዎችን፣ የፍጆታ ዕቃዎችን እና የህክምና መሳሪያዎችን እንዳካተተ የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የዚምባብዌ... 02.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-02T15:53+0300
2024-08-02T15:53+0300
2024-08-02T16:23+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий