የሐምሌ 26 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የሐምሌ 26 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 በሩሲያ ቤልጎሮድ ግዛት ሼቤኪንስኪ አውራጃ በዩክሬን ድሮኖች በደረሰ ጥቃት ሁለት ንፁሀን ዜጎች መቁሰላቸውን የአከባቢው አስተዳዳሪ አስታውቀዋል። በአንድ ሌሊት ስድስት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በኩባን እና ኩርስክ ክልሎች መውደም እና መጨናገፋቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አመልከቷል። 🟠 የአታካምስ ሚሳኤል ከፍተኛ ፈንጂ ክፍል በሩሲያ ሴቫስቶፖል ባለ 9 ፎቅ ህንፃ ላይ ወድቆ እንደነበር የገለጹት የክልሉ ገዥ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን እና ነዋሪዎች ከአካባቢው እንዲለቁ እየተደረገ መሆኑን ገዥው ዘግቧል። 🟠 በደርዘን የሚቆጠሩ ሩሲያውያን በአሜሪካ እስር ቤቶች እንደሚገኙ እና ዲፕሎማቶች ለማስፈታት የተቻለውን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርጉ በአሜሪካ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ አስታወቀ። 🟠 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባይደን ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጋር አሜሪካ እስራኤልን ለመደገፍ "አዲስ የመከላከያ ወታደራዊ ስምሪቶችን" በምትልክበት መንገድ ዙርያ ተወያይተዋል። 🟠 ሩሲያዊው ጠፈርተኛ ኪሪል ፔስኮቭ እ.አ.አ በየካቲት 2025 በአሜሪካ ድራጎን የጠፈር መንኮራኩር ወደ ዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ እንደሚበር ሮስኮስሞስ ዘግቧል። በናሳ እና በሮስኮስሞስ መካከል የእርስ በርስ በረራዎችን በተመለከተ ስምምነት አለ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0