ሩሲያ ከካዛኽስታን ይልቅ ወደ አፍሪካ ሀገራት የእህል አቅርቦት ልትልክ እንደምትችል አንድ ባለሙያ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ ከካዛኽስታን ይልቅ ወደ አፍሪካ ሀገራት የእህል አቅርቦት ልትልክ እንደምትችል አንድ ባለሙያ ተናገሩ ይህ ካዛኽስታን በሩሲያ የስንዴ ኢምፖርት ላይ የጣለችውን እገዳ ማራዘሟን ተከትሎ የመጣ ነው። ገለልተኛ የኢንደስትሪ ኤክስፐርት የሆኑት ሊዮኒድ ካዛኖቭ እንዳሉት ከሩሲያ ወደ ካዛኽስታን የሚላከው የእህል መጠን ቢያንስ በዓመት 1.5 ሚልዮን ቶን ሊገመት የሚችል ሲሆን የካዛኽስታን እህል ምርት በዓመት ከ16 ሚሊዮን ቶን ይበልጣል። "የካዛኽስታን መንግሥት ውሳኔ ለ [ሩሲያ] ገበሬዎች ጥሩ ባይሆንም አደገኛ ግን አይደለም፤ ለሌሎች ሀገሮች ለምሳሌ ለአፍሪካ ሀገራት የእህል ሽያጫቸውን መጨመር ይችላሉ" ብለዋል። በማዕከላዊ እስያዊቷ ሀገር በሩሲያ ስንዴ ላይ የተጣለው የኢምፖርት ገደብ የጀመረው በሚያዝያ 2023 ነበር። ቀደም ሲል ካዛኽስታን እስከዚህ ዓመት መጨረሻ ድረስ እገዳውን ማራዘሟን አስታውቃለች። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0