ፕሪቶሪያ የሐማስ ፖሊት ቢሮ መሪ እስማኤል ሃኒዬን ግድያ አወገዘች "መንግሥት ለሃኒዬ ቤተሰብ እንዲሁም ለፍልስጤም አመራሮች እና ህዝቦች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል። ደቡብ አፍሪካ የዶ/ር ሃኒዬ ግድያ እና በጋዛ በሲቪሎች ላይ የቀጠለው ጥቃት ቀድሞውንም ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የነበረውን ሁኔታ የበለጠ እንዳያባብሰው አሳስቧታል" ሲል የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ገልጿል። ጥብቅ ምርመራ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት የሰጠው የሚኒስቴሩ መግለጫ “አደገኛ ሁኔታ ውስጥ በሚገኘው ክልል ውሰጥ ውጥረቶችን ከሚያባብሱ ማንኛውም ድርጊቶች ሁሉም አካላት እንዲቆጠቡ” ጠይቋል። "እንዲህ ያሉ ከሕግ ውጪ የሚፈፀሙ ግድያዎች ዓለም አቀፍ ሕግን እና የሰብዓዊ መብት መርሆዎችን የሚጥሱና በመካከለኛው ምስራቅ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ያዳክማሉ። የትኛውም ሀገር ከሕግ በላይ አይደለም እናም ሁሉም ሀገራት የዓለም አቀፍ ሕግን በተለይም በተባበሩት መንግሥታት ቻርተር እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕጎች ስር የተዘረዘሩትን መርሆዎች ሊያከብሩ ይገባል" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሮናልድ ላሞላ ተናግረዋል። የደቡብ አፍሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አክሎም "ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በጋዛ ላይ እየደረሰ ያለውን የዘር ጭፍጨፋ ለማስቆም፣ ተጠያቂነትን ለማስፍን፣ ፍልስጤማውያን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት እና እስራኤል የምትፈጽመውን ሕገ-ወጥ ወረራ ለማስቆም አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባል" ብሏል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ፕሪቶሪያ የሐማስ ፖሊት ቢሮ መሪ እስማኤል ሃኒዬን ግድያ አወገዘች
ፕሪቶሪያ የሐማስ ፖሊት ቢሮ መሪ እስማኤል ሃኒዬን ግድያ አወገዘች
Sputnik አፍሪካ
ፕሪቶሪያ የሐማስ ፖሊት ቢሮ መሪ እስማኤል ሃኒዬን ግድያ አወገዘች "መንግሥት ለሃኒዬ ቤተሰብ እንዲሁም ለፍልስጤም አመራሮች እና ህዝቦች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል። ደቡብ አፍሪካ የዶ/ር ሃኒዬ ግድያ እና በጋዛ በሲቪሎች ላይ የቀጠለው ጥቃት... 01.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-01T16:26+0300
2024-08-01T16:26+0300
2024-08-01T16:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий