የሐማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒዬ ግድያ የዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው ስትል ሶማሊያ አወገዘች "ሶማሊያ ግጭቱ እየተባባሰ የመጣበት ፍጥነት ሲቪሎች ላይ ተጨማሪ ጥሰቶችን ሊያስከትል የሚል ስጋት አላት" ሲል የገለጸው የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፍልስጤም ህዝብ የተሰማንን "ከልብ የመነጨ ሀዘን" እንገልፃለን ብሏል። ሐማስ ሃኒዬ በቴህራን የኢራን አዲሱ ፕሬዝዳንት የሹመት ስነ-ስርዓት ላይ በተገኙበት ወቅት ለተፈፀመው ጥቃት እስራኤልን ተጠያቂ ቢያደርግም እስራኤል ሃላፊነት ከመውሰድም ሆነ ከማስተባበል ተቆጥባለች። የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ "ኃላፊነቱን እንዲወጣ እና እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርሰውን ጥቃት እና በዓለም አቀፍ ህግና የተባበሩት መንግስታት ውሳኔዎች ላይ የምትፈፅመውን ጥሰት ለማስቆም አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።" በሃኒዬ ላይ የተፈፀመው ጥቃት እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለውን ጥቃት ተከትሎ የመጣ ነው። በጥቃቱ ወደ 40,000 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን ሲቪሎች በአብዛኛው ሴቶች እና ህጻናት መሞታቸውን የጋዛ የጤና ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ግጭቱ አብዛኛው የጋዛ ሰርጥ ክፍልን ያፈራረሰ ሲሆን መጠነሰፊ ዓለም አቀፍ ውግዘትንም አስከትሏል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሐማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒዬ ግድያ የዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው ስትል ሶማሊያ አወገዘች
የሐማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒዬ ግድያ የዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው ስትል ሶማሊያ አወገዘች
Sputnik አፍሪካ
የሐማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒዬ ግድያ የዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው ስትል ሶማሊያ አወገዘች "ሶማሊያ ግጭቱ እየተባባሰ የመጣበት ፍጥነት ሲቪሎች ላይ ተጨማሪ ጥሰቶችን ሊያስከትል የሚል ስጋት አላት" ሲል የገለጸው የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር... 01.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-01T14:02+0300
2024-08-01T14:02+0300
2024-08-01T14:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የሐማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒዬ ግድያ የዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው ስትል ሶማሊያ አወገዘች
14:02 01.08.2024 (የተሻሻለ: 14:40 01.08.2024)
ሰብስክራይብ