የስፑትኒክ ኢትዮጵያ የሐምሌ 21 ረፋድ አጫጭር ዜናዎች፡- 🟠 ቬኔዙዌላውያን በሀገሪቱ ተቃዋሚዎች፣ ሲቪል ማህበረሰብ እና ዓለም አቀፍ ተዋናዮች የቅርብ ክትትል ስር አዲስ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ እሁድ ወደ ምርጫ ጣቢያ ያቀናሉ። 🟠 የአሜሪካ ባለስልጣናት በጎላን ተራሮች ላይ የተፈፀመው ጥቃት እስራኤልን እና የሊባኖሱ ሄዝቦላን ወደ ሙሉ ጦርነት ሊሰድ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣናትን ጠቅሰው ዘግበዋል። 🟠 የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር እስራኤል ካትዝ በጎላን ተራሮች ለደረሰው ጥቃት ምላሽ እንደሚሰጥ ዝተው ሀገራቸው ከሄዝቦላ እና ሊባኖስ ጋር ሙሉ ጦርነት ለመጀመር እንደተቃረበች ተናግረዋል። 🟠 ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ከተደረገ ሁለት ሳምንት በኋላ የቀድሞው ፕሬዝዳንት በጥይት ወይም በአንዱ ስባሪ ተመትተዋል ሲል የፌደራል የምርመራ ቢሮ አስታውቋል። መግለጫው የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ክሪስቶፈር ሬይ ትራምፕ በተኩሱ ወይም በፍንጣሪው ይመቱ ግልጽ አይደለም ብለው ውዝግብ ካስነሱ በኋላ የመጣ ነው። 🟠 የአሜሪካ እና ጃፓን ባለስልጣናት በጃፓን አዲስ የአሜሪካ ወታደራዊ እዝ መቋቋሙን ያስታውቃሉ ሲሉ ምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። አዲሱ እዝ “የቻይናን ወታደራዊ ዝግጅት” መነሻ አድርጎ እንደሚቋቋም ተገልጿል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የስፑትኒክ ኢትዮጵያ የሐምሌ 21 ረፋድ አጫጭር ዜናዎች፡-
የስፑትኒክ ኢትዮጵያ የሐምሌ 21 ረፋድ አጫጭር ዜናዎች፡-
Sputnik አፍሪካ
የስፑትኒክ ኢትዮጵያ የሐምሌ 21 ረፋድ አጫጭር ዜናዎች፡- 🟠 ቬኔዙዌላውያን በሀገሪቱ ተቃዋሚዎች፣ ሲቪል ማህበረሰብ እና ዓለም አቀፍ ተዋናዮች የቅርብ ክትትል ስር አዲስ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ እሁድ ወደ ምርጫ ጣቢያ ያቀናሉ። 🟠 የአሜሪካ ባለስልጣናት... 28.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-28T12:50+0300
2024-07-28T12:50+0300
2024-07-28T13:20+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий