የዚምባብዌ ቀዳማዊት እመቤት ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ እርሻ የተላከ ድንች ደረሳቸው በሐምሌ ወር መጀመሪያ ቤላሩስን የጎብኙት ኦክሲሊያ ምናንጋግዋ ከሉካሼንኮ ጋር ተገናኝተው ነበር። በዚህ ሳምንት መገባደጃ የቤላሩስ ሴቶች ህብረት የልዑካን ቡድን በቀዳማዊት እመቤቷ ግብዣ ዚምባብዌን ጎብኝቶ በአፍሪካ ሴቶች ፎረም ላይ ተሳትፏል። "ከሚንስክ እስከ ዚምባብዌ ቪክቶሪያ ፏፏቴ ድረስ ከስድስት ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የተጓዘው እጅግ ዋጋ ያለው ጭነት ዛሬ ለተቀባዩ ደርሷል- ከቤላሩስ መሪ እርሻ የተላከ ድንች ለቀዳማዊት እመቤት ተላልፏል። ኦክሲሊያ ምናንጋግዋ ቤላሩስን በጎበኙበት ወቅት በጣም የወደዷቸው 'ፐርሻትስቬት' እና 'ማኒፌስት' የተባሉ ታዋቂ ዝርያዎች ናቸው" ሲሉ የቤላሩስ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የአዲሱ ሰብል ድንቾች በሁለት ልዩ የእንጨት ሳጥኖች ውስጥ እንደደረሱ ዘገባው አመላክቷል። ድንቾቹ ለመብል እንደሚሆኑ እና ለተክል የሚሆኑ የድንች ዘሮች በቅርቡ ወደ ዚምባብዌ እንደሚላኩ ተገልጿል። ቀዳማዊት እመቤቷ በበኩላቸው ዚምባብዌ ውስጥ የሚተዋወቀው የቤላሩስ ድንች በጥሩ ሁኔታ ይበቅላል የሚል እምነታቸውን ገልጸዋል። ለጨዋታም የድንች ዝርያው ዚምባቡዌ ነው ወይስ ቤላሩስ የተሻለ የሚያድገው ብለው ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮን ውርርድ ገጥመዋል። ከቤላሩስ የግብርና ምርቶች በተጨማሪ ዚምባብዌ የቤላሩስ የቤት ዕቃዎችን፣ ቀላል የኢንዱስትሪ ምርቶችን እና የእንግዳ መስተንግዶ ኢንዱስትሪ መዋቢያዎችን እንደምትፈልግ የቤላሩስ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የዚምባብዌ ቀዳማዊት እመቤት ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ እርሻ የተላከ ድንች ደረሳቸው
የዚምባብዌ ቀዳማዊት እመቤት ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ እርሻ የተላከ ድንች ደረሳቸው
Sputnik አፍሪካ
የዚምባብዌ ቀዳማዊት እመቤት ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ እርሻ የተላከ ድንች ደረሳቸው በሐምሌ ወር መጀመሪያ ቤላሩስን የጎብኙት ኦክሲሊያ ምናንጋግዋ ከሉካሼንኮ ጋር ተገናኝተው ነበር። በዚህ ሳምንት መገባደጃ የቤላሩስ ሴቶች ህብረት... 28.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-28T10:18+0300
2024-07-28T10:18+0300
2024-07-28T10:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የዚምባብዌ ቀዳማዊት እመቤት ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ እርሻ የተላከ ድንች ደረሳቸው
10:18 28.07.2024 (የተሻሻለ: 10:40 28.07.2024)
ሰብስክራይብ