የብሪክስ ሙፍቲዎች ሩሲያ ካዛን በተካሄደው ፎረም መንፈሳዊ ውይይት አካሄዱ ለመንፈሳዊ የሲልክ ሮድ መድረክ በካዛን የተሰባሰቡ የብሪክስ ሙፍቲዎች ሐይማኖታዊ ውይይቶችን በድርጅቱ ማዕቀፍ ውስጥ ለማስፋት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። የቁርዓን ንባብ ውድድርን ባካተተው ፎረም ከሩሲያ ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፣ ኢራን ፣ ግብፅ ፣ ቻይና ፣ ብራዚል ፣ ኢትዮጵያ ፣ ህንድ እና ከደቡብ አፍሪካ የመጡ የሐይማኖት መሪዎች የትብብር ሰነድ ፈርመዋል። ይህ ትብብር መንፈሳዊ እና ሥነ ምግባራዊ እሴቶችን እንዲሁም የቤተሰብ እሴቶችን መጠበቅ፣ ትውልድ ሀገርን መውደድ እና ጽንፈኝነትን እና ሽብርተኝነትን መቃወም ላይ ያተኩራል። ከብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ በፊት የተካሄደው የፊርማ ስነ-ስርዓት የሐይማኖት መሪዎቹ ለአባል ሀገራቱ መሪዎች ያደረጉት ምርቃት እንደሆነ ተቆጥሯል። ሐይማኖታዊ ውይይት እና መግባባትን ለማበረታታት ያለመውን መንፈሳዊ የሲልክ ሮድ ፕሮጀክት የብሪክስ ሃገራት የሙስሊም ማህበረሰብ ተሳታፊዎች አወድሰውታል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የብሪክስ ሙፍቲዎች ሩሲያ ካዛን በተካሄደው ፎረም መንፈሳዊ ውይይት አካሄዱ
የብሪክስ ሙፍቲዎች ሩሲያ ካዛን በተካሄደው ፎረም መንፈሳዊ ውይይት አካሄዱ
Sputnik አፍሪካ
የብሪክስ ሙፍቲዎች ሩሲያ ካዛን በተካሄደው ፎረም መንፈሳዊ ውይይት አካሄዱ ለመንፈሳዊ የሲልክ ሮድ መድረክ በካዛን የተሰባሰቡ የብሪክስ ሙፍቲዎች ሐይማኖታዊ ውይይቶችን በድርጅቱ ማዕቀፍ ውስጥ ለማስፋት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። የቁርዓን ንባብ ውድድርን... 28.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-28T09:24+0300
2024-07-28T09:24+0300
2024-07-28T09:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий