በኒያሚ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች በሩሲያ መዝሙር ተከፈቱ

ሰብስክራይብ
በኒያሚ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች በሩሲያ መዝሙር ተከፈቱ እጅ-ለእጅ በህብረት ኒጀር-ሩሲያ የተሰኘውን ግብረሰናይ ድርጅት የሚመሩት ሙሃማዱ ዲኮ ለስፑትኒክ የተናገሩት ነው። "አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በሩሲያኛ መዝሙር እያስጀመርን ነው። በሁሉም ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብርራችን ማዳበር አለብን። ኒጀር ከሩሲያ ጋር ወዳጅነት መመሥረት የምትፈልግ ልዩ ተስፋ ያላት ሀገር ነች" ሲሉ አብራርተዋል። በዚህ የግብረሰናይ ድርጅት ድጋፍ ከተማዋን ለማጽዳትና የሕዝብ ቦታዎችን ለማሻሻል ፕሮጀክቶች ይጀመራሉ። "አንዳንድ ሀገራት የኒጀር ህዝብ ሉዓላዊነታቸውን ለማስከበር በሚያደርጉት ትግል ህገ-ወጥ እና አፍራሽ ማዕቀቦችን ቢጥሉም ሩሲያ ከኒጀር ጎን ቆማለች። የኒጀር ህዝብ በዚህ ትብብር ደስተኛ ነው" ሲሉ በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኒያሚ ከንቲባ ቡባካር ሱማና ጋራንኬ አክለዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0