ዩኔስኮ የሴኔጋል ኒዮኮሎ-ኮባ ብሔራዊ ፓርክን አደጋ ውስጥ ካሉ የዓለም ቅርስ መዝገብ ዝርዝር አስወጣ ውሳኔው የተላለፈው በዚህ ሳምንት በኒው ዴልሂ ህንድ ተካሄዶ በነበረው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነው። የፓርኩን የብዝሃ ህይወት ስጋት በመቅረፍ ሴኔጋል ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቷን ተከትሎ ፓርኩ ከዝርዝሩ ውስጥ መውጣት እንደቻለ ድርጅቱ አስታውቋል። በጋምቢያ ወንዝ አቅራብያ የሚገኘው ፓርክ የዓለማችን ትልቁን አጋዘን ጨምሮ የተለያዩ የዱር እንስሳት መገኛ ነው። በአደን፣ የማዕድን ቁፋሮ እና ሌሎች አስጊ የሰዎች እንቅስቃሴ ምክንያት እ.አ.አ. በ2007 አደጋ ውስጥ ከሚገኙ የዓለም ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ ተካቶ ተከታታይ የጥበቃ እርምጃዎች በአፋጣኝ እንዲተገበር ተደርጓል። "ምልክት የሆኑ ዝርያዎችን የመከታተል ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል...ህገ-ወጥ አደን፣ ህገ-ወጥ የወርቅ እጥበትን ለመከላከል እንዲሁም የከብቶችን ስምሪት ለማደራጀት ለፓርኩ ክትትል ከፍተኛ ሀብት ተመድቧል" ሲል ዩኔስኮ አስታውቋል። በተጨማሪም ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር በማዕድን አወጣጥ ሂደት የሚደርሰውን ብክለት ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራር መዘርጋቷንም ዓለም አቀፉ ድርጅት አመልክቷል። ሴኔጋል ከ913,000 ሄክታር በላይ የሚሸፍነውን ታዋቂ ፓርክ ሥነ-ምህዳር ከሚያጠቃው ወራሪ የሚሞሳ ፒግራ ተክል ዝርያን ለመዋጋት ያደረገችውን ጥረት ዩኔስኮ አሞግሷል። እ.አ.አ. በ1981 በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበውን የኒዮኮሎ-ኮባ ብሔራዊ ፓርክ የረጅም ጊዜ ደህንነት ለማረጋገጥ ሴኔጋል በሚቀጥሉት ዓመታትም ጥረቷን እንድትቀጥል የዓለም ቅርስ ኮሚቴ አሳስቧል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ዩኔስኮ የሴኔጋል ኒዮኮሎ-ኮባ ብሔራዊ ፓርክን አደጋ ውስጥ ካሉ የዓለም ቅርስ መዝገብ ዝርዝር አስወጣ
ዩኔስኮ የሴኔጋል ኒዮኮሎ-ኮባ ብሔራዊ ፓርክን አደጋ ውስጥ ካሉ የዓለም ቅርስ መዝገብ ዝርዝር አስወጣ
Sputnik አፍሪካ
ዩኔስኮ የሴኔጋል ኒዮኮሎ-ኮባ ብሔራዊ ፓርክን አደጋ ውስጥ ካሉ የዓለም ቅርስ መዝገብ ዝርዝር አስወጣ ውሳኔው የተላለፈው በዚህ ሳምንት በኒው ዴልሂ ህንድ ተካሄዶ በነበረው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነው። የፓርኩን የብዝሃ ህይወት ስጋት... 27.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-27T11:20+0300
2024-07-27T11:20+0300
2024-07-27T11:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ዩኔስኮ የሴኔጋል ኒዮኮሎ-ኮባ ብሔራዊ ፓርክን አደጋ ውስጥ ካሉ የዓለም ቅርስ መዝገብ ዝርዝር አስወጣ
11:20 27.07.2024 (የተሻሻለ: 11:40 27.07.2024)
ሰብስክራይብ