ደቡብ አፍሪካ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ ከሩሲያ እና የብሪክስ አጋሮች ጋር የንግድ ልውውጥ መጨመር እንደምትፈልግ ምክትል የንግድ ሚኒስትሩ ገለፁ ሚኒስትሩ ዙኮ ጎድሊምፒ ሁለቱ የብሪክስ አባል ሀገራት ታዳጊ ሀገራትን በተሻለ መልኩ የሚወክል ፍትሃዊ የዓለም የንግድ ስርዓት ለመገንባት የጋራ ግብ እንዳላቸው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስአስታውቀዋል። በብሪክስ ሀገራት መኻከል በተለይም ለግብርና እና ኢነርጂ ዘርፎች ጠንካራ የአቅርቦት ሰንሰለት በመገንባት ረገድ ትብብርን ማሳደግ ጠቀሜታ እንዳለው አመልክተዋል። "ሩሲያ በጋዝ ሃይል በማመንጨት የቆየ አቅም አላት፤ ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ከኃይል ዋስትና ስጋቶች ጋር እየታገለች ነው" ብለዋል ጎድሊምፒ። "ከሩሲያውያን ጋር ሰኬታማ ውይይት ለማድረግ ከምንሻባቸው አንዱ የትብብር ዘርፍ ነው።" በተጨማሪም ከፍተኛ የግብርና ምርት የንግድ ልውውጥ አቅም እንዳለ ጠቁመው ደቡብ አፍሪካ ለሩሲያ ገበያ ምርት ማቅረብ እንደምንችል ተናግረዋል። ጎድሊምፒ አክለውም በዓለም አቀፍ ደረጃ የአረንጓዴ ሽግግር እየተካሄደ ባለበት ወቅት በኢነርጂ ዘርፍ የቴክኖሎጂ ልውውጥ እና የኢንቨስትመንት እድሎችን የመጠቀም አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተዋል። "የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ እድገታችን ቁልፍ ጉዳይ ለደቡብ አፍሪካ ምርቶች አማራጭ ገበያ መፍጠር ነው" ያሉት ሚኒስትሩ "ብሪክስ የገበያ መዳረሻችንን ለማስፋት ጥሩ መነሻ ነው" ሲሉም አብራርተዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ደቡብ አፍሪካ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ ከሩሲያ እና የብሪክስ አጋሮች ጋር የንግድ ልውውጥ መጨመር እንደምትፈልግ ምክትል የንግድ ሚኒስትሩ ገለፁ
ደቡብ አፍሪካ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ ከሩሲያ እና የብሪክስ አጋሮች ጋር የንግድ ልውውጥ መጨመር እንደምትፈልግ ምክትል የንግድ ሚኒስትሩ ገለፁ
Sputnik አፍሪካ
ደቡብ አፍሪካ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ ከሩሲያ እና የብሪክስ አጋሮች ጋር የንግድ ልውውጥ መጨመር እንደምትፈልግ ምክትል የንግድ ሚኒስትሩ ገለፁ ሚኒስትሩ ዙኮ ጎድሊምፒ ሁለቱ የብሪክስ አባል ሀገራት ታዳጊ ሀገራትን በተሻለ መልኩ የሚወክል ፍትሃዊ የዓለም... 26.07.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-07-26T20:02+0300
2024-07-26T20:02+0300
2024-07-26T20:40+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ደቡብ አፍሪካ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ ከሩሲያ እና የብሪክስ አጋሮች ጋር የንግድ ልውውጥ መጨመር እንደምትፈልግ ምክትል የንግድ ሚኒስትሩ ገለፁ
20:02 26.07.2024 (የተሻሻለ: 20:40 26.07.2024)
ሰብስክራይብ